የአርባ ምንጭ –ጂንካ መንገድ ተዘጋ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የአርባ ምንጭ –ጂንካ መንገድ ተዘጋ
ዛሬ የካቲት 25/08 በኮንሶ ከተማ የመከላከያ ኃይል ከህዝቡ ጋር በፈጠረው ግጭት የኮንሶ ልዩ ወረዳ ዋና ከተማ ካራት ውስጥ የጥይት ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡ ወደከተማዋ ደውለን ባገኘነው መረጃ መሰረት ግጭቱ የተነሳው እስከ ፌዴሬሽን ም/ቤት የደረሰውን የአካባቢው ህዝብ ያቀረበው ህገመንግስታዊ የአከላለል ጥያቄ ለማፈን የሄደውና ለወራት በአካባቢው ሰፍሮ የሚገኘው የደቡብ ልዩ ኃይል በአካባቢው የህዝብ ጥያቄውን ለመንግስት እንዲያቀርቡ የተወከሉት የአገር ሽማግሌዎች/ ተወካዮች ሰብሳቢ አቶ ገዛሃኝ ገላ ቤት በመሄድ አስገድደው ይዘው ሲወጡ ህዝቡ ባሰማው ተቃውሞ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ህዝቡ ለማስለቀቅ ቢሞክርም ታጣቂ ኃይሉ ጥይት ወደ ህዝቡ በመተኮስ ከበተኑ በኋላ አቶ ገዛሃኝን ይዘው በመሄዳቸው ህዝቡተበተቃውሞው ቀጥሎበታል፡፡ ይህንኑ ግጭት ተከትሎ ተጨማሪ ታጣቂ ኃይል በ11 ሰዓት ደቡብ ፖሊስ በሚሉ መኪናዎች ከተማዋ እንደደረሰ ተረጋግቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ታጣቂ ኃይሉ ህዝቡን ለማስፈራራት ጥያቄውንም ከተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ለማያያዝ እየሞከረ ሲሆን በዚህ መሰረት በምርጫ 2007 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የነበሩት አቶ አክሊሉ….. ቤታቸውን እንደተከበበ እርሳቸውም ቤታቸው ሆነው የሚመጣውን ለመጠበቅ እንደተገደዱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የተኩስ ድምጽ የሰሙ በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ የገጠር ነዋሪዎች የከተማውን ህዝብ ተቀላቅለዋል፡፡ ከዚሁ ግጭት በተያያያዘ ከተማዋን አቋርጦ የሚያልፈው የአርባ ምንጭ–ጂንካ መንገድ የተዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ከየቱም አቅጣጫ ወደ ከተማዋ የሚመጡ መኪናዎች ፊታቸውን እያዞሩ ወደመጡበት ለመመለስ ተገደዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ አቶ አክሊሉ—- 0913 857984