የአዲስ አበባ ታክሲዎች አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ አሽከርካሪዎች በአድማው እየተሳተፉ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የአዲስ አበባ ታክሲዎች አድማ ተከትሎ በኦሮሚያ አሽከርካሪዎች በአድማው እየተሳተፉ ነው::
#Ethiopia #Oromoprotests #TaxiDriversStrike #AddisAbaba #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኦሮሚያ የአውቶብስ መናኽሪያዎች ባዶ ሆነዋል::በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የታክሲዎች የስራ ማቆም አድማ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተስፋፍቶ በዛሬው እለት በወሊሶ በሆለታ ኢጂራ ጊንጪ አምቦ ጉደር ኤዶ ባኮ የሕዝብ ትራንስፖት የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ትራንስፖርት አለመኖሩ ተረጋግጧል:: አንድ ከአዲስ አበባ የተላከ የመንግስት አዉቶቡስ ከወሊሶ መናሀሪያ ሰዎችን ሊጭን ከተማዋ እንደደረሰ ባልተወቁ ሀይሎች ጥቃት ተፈጽሞበት ከጥቅም ውጪ ስለሁን ተልኮው ተስተጓጉሏል። ሾፌሩ እና ረደቱ ያለምንም ጉዳት ሄደዋል::የአምቦ መናሀሪያ አፉን ከፍቶ ባዶውን ውሏል።
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀረሳ ወረዳ በቀርሳ ከተማ እና በቀርሳ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎች ህዝቡ ተቃውሞን በማሰማት ላይ እያለ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት የሃይል እርምጃ እስካሁን 2 ሰዎች የሞቱ እና ብዛት ያላቸው እንደቆሰሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። በዛሬው እለት በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ አንደኛ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ እና የቴክኒክ እና ሙያ ተማሪዎች ከአሁን ቡሃላ አንማር ብለው ትምርት ትተው ወደቤታቸው ተመልሰዋል ።አሙሩ ወረዳ ባለፉት 4 ወራት በተከታታይ ተቃውሞ ሲሰማበት የነበረ ወረዳ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ
