የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግብርና ፑል ንብረት በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግብርና ፑል ንብረት በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ በጎጃም የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግብርና ፑል ንብረት መጋዘን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ዛሬ የካቲት 20/2008 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ጀምሮ ወደመ፡፡ መጋዘኑ የ 5 ጽ/ቤቶች ( ማለትም ግብርና፡ ውሃ፡ ህብረት ሥራ ማህበራት፡ አካባቢ ጥበቃና የገጠር መንገድ) ጽ/ቤቶች በጋራ የሚጠቀሙበት በታም ግዙፍ መጋዘን ሲሆን በውስጡም የ2008ዓ.ም የገጠርና ከተማ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ማቴሪያል፡ የግብርና ግባቶች፡ የዕርዳታ እህል፡ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ ንብረቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡
በዚህ ጉዳት ከ 30 ሚሊዮን በላይ ግምት ያለው የወረዳው ሀብት የወደመ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ በትክክል የታወቀ ባይሆንም ከአስተዳደሩ ሰራተኞች የሆኑት የብአዴን አባላት የዘረፉትን የህዝብ ሀብት ዘረፋ ጋር በተያያዘ መረጃ ለማጥፋት ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ህብረተሰቡ በይፋ በናገር ላይ ነው፡፡ቃጠሎው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የአካባቢው ህ/ሰብ ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
Source- Facebook

