በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ ሌሎችንም ብሄሮች እንዳካተተ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ ሌሎችንም ብሄሮች እንዳካተተ ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::
#Ethiopia #Oromoprotests #EthiopianOppositionparties #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – Ethiopian DJ – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለው ሕዝባዊ የተቃውሞ ድምጽ በዛሬው እለት በወለጋ በሃረርጌ በሸዋ በኢሊባቦር እና በተለያዩ አከባቢዎች ሕዝቡ ከባድ ተቃውሞ ሲያሰማ ውሏል::በማለዳው በቦረና ያቤሎ ከተማ የጀመረው ተቃውሞ ሕዝቡ በነቀስ ወጥቶ ተቃውሞውን ያሰማ ሲሆን ደምየጠማቸው ሰው በላዎቹ አግኣዚዎች የሶሩዱ የቢሮ ሃላፊን አቶ ከድር አብዶን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ ጉዳት አድርሰዋል::
በወለጋ ቀለም ጊዳሜ ወረዳ ወሪ ቀበሌ የአንባገነኑ መንግስት 5 ሰዎችን መግደሉን እና በርካቶች ማቁሰሉ ተሰምቷል::በምዕራብ ወለጋ ዩብዶ ወረዳ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እየተደረገ ሲሆን ወረዳዋ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ ሃብት ቢኖራትም የአካባቢው ህብረተሰብ የሀብቱ ተጠቃሚ አለመሆኑና በችግር ላይ የሚገኝ መሆኑ እንዲሁም የሀብቱ ተጠቃሚ አንድ ባለሃብት ብቻ መሆኑ የታወቀ ሲሆን በዛሬው እለት እየተደረገ ያለው ተቃውሞም የመጀመሪያው አለመሆኑ ታውቋል ። በምዕራብ ወለጋ አይራ ከተማ ከፍተኛ የሆነ ታቃውሞ የአካባቢው ነዋሪዎች በማድረግ ላይ መሆናቸው ታወቀ ።የአካባቢው ነዋሪዎች ትግሉ ከተጀመረ ጀምሮ በተቃውሞው ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ እርምጃዎች ቢወሰድባቸውም ትግሉን አፋፍመው ከመቀጠል ወደኃላ አለመላታቸው ታውቋል ።
ምእራብ ሃረርጌ ጋዲሎ ተቃውሞ የተሰማ ሲሆን በበደኖ ሶስት ቀን መንገድ ተዘግቶበት የነበረው የአግኣዚ ጦር በሰባት ካሚዮኖች ተጭኖ ወደ ከተማው ገብቷል:: በምዕራብ ሃረርጌ የዳሩ ለቡ ወረዳ ነዋሪዎች: ትጨርሱናላችሁ እንጂ በፍፁም አትገዙንም በማለት በወረዳው ውስጥ በሚገኙ መቻ ፣ ሚጨታ ፣ ቢልቃዔ ፣ ጋዱሎ ፣ በሚባሉ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ በቀን በለሊት እያደረጉ መሆናቸው ታወቀ ።ተቃውሞውን አቀጣጥለው የቀጠሉት ታጋዮቹ የዳሩ ለቡ ወረዳ ነዋሪዎች :በጎሎልቻ ፣ ሃብሮ እና አንቻር : አካባቢ ያሉ ወገኖችም እንደተለመደው ከጎናቸው በመቆም ትግሉን እንዲያፋፍሙ ጥሪ አቅርበዋል ።በመጀራ ከሁለት ቀን በፊት አስራ አራት ሰዎች በአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውም የሚታወስ ነው ።በሸዋ ቤላሚ ከተማ በኢሊባቦር በበደሌ ከተማ ኢሉ አባቦራ ዞን ተማሪዎች ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሲሆን የበደሌ ቢራ ፋብሪካ መኪና ላይም ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል::
በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ያለው እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ የቆመ ሲሆን የወያኔ መንግስት በቦታው የነበሩ ፖሊሶችን ትጥቃቸውን በማስፈታት ባዶ እጃቸውን እንዳስቀራቸውና በአካባቢውም የአጋዚ ጦርንና ከሱማሌ ክልል የሆኑ ወታደሮችን ማስፈሩ ታውቋል ።
በተያያዘ ዜናም ሞሉ ሃለኬ የተባለውን ተማሪ ጢሌ ቀበሌ ላይ በዛሬው እለት የቀበሌው አስተዳዳሪ የሆነው ከነዮ ዋሪዮ የሚባለው አንተ አሸባሪ የኦነግ አባል ነህ ካለው በኃላ ለወያኔ ወታደሮች በመናገሩ ወታደሮችም አፍነው ከወሰዱት በኃላ ከባድ ማስጠንቀቂያ ከሰጡት በኃላ እንደለቀቁት ታውቋል ።