የፍትህ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው ብለሃል በሚል ሰበብ የፖለቲካ ድርጅት መሪ በጅንካ ታሰሩ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


https://fbcdn-profile-a.akamaihd.net/hprofile-ak-frc3/v/t1.0-1/p160x160/1958275_1573257959575607_871358952806069033_n.jpg?oh=6a2ed0bac5bd788148a677a6f01c00d6&oe=576775E0&__gda__=1465588338_e568ca19dfb2cdf7b5e7a50fddc8e903የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ ምክትል ሊቀመንበር ታሰሩ// አቶ ዓለማዬሁ መኮንን የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ ኦህዲኅ/ ምክትል ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ‹‹ የፍትህ ጥያቄ – የነጻነት ጥያቄ ነው ›› በማለት ተናግረዋል በሚል ዛሬ በፖሊስ ተይዘው ለእስር መዳረጋቸውን የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፖሊስ ደብዳቤ ይዞ ቢያስራቸውም ቃላቸውን ያልተቀበለና በጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ታዘን ነው በሚል ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት አቅርቧቸው ትዕዛዝ ሰጡ የተባሉት ዳኛ ዳዊት አድማሱ ጥሩነህ ‹‹ እኔ አላዘዝኩም፣ በማን ትዕዛዝ እንደታሰሩ ከከንቲባው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጋር ተነጋግረን መልስ እንሰጣለን፣ለጊዜው ከእንግዳ ጋር ናቸው ›› በማለታቸው ያለከሳሽ፣ በዕለት ሁኔታ መዝገብ ሳይመዘገቡና ቃላቸውን ሳይሰጡ እንዲሁም ጥፋታቸው ወይም የተጠረጠሩበት ወንጀል እንኳ ሳይነገራቸው በእስር ቤት እንዲያድሩ ተደርገዋል ፡፡ በአቶ እንዲሪስ መናን የዞኑ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ የሚመሩ የትግል ጓዶቻቸው የአቶ ዓለማዬሁን እስራት ሁኔታ ለመከታተል ባደረጉት ጥረት የከተማውን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተፈራ ሥዩም አነጋግረው የታሰሩት በፍ/ቤት ትዕዛዝ ነው ይበሉ እንጂ ጥፋታቸውን ሊነግሯቸው እንዳልቻሉ፣ ዳኛ ዳዊትም እሳቸው ምንም ትዕዛዝ እንዳልሰጡ ለምንና በማን እንደታሰሩ እንደማያውቁ እንደነገሯቸው ገልጸዋል ፡፡

ቶ እንዲሪስ ስለሁኔታው ሲያብራሩ በመጀመሪያ አቶ ዓለማዬሁ አሉ የተባለው ‹‹የፍትህ ጥያቄ – የነጻነት ጥያቄ ነው ›› የሚለው ትክክልና በህግ የማያስጠይቅ ሲሆን ፖሊስና ፍርድ ቤት ጉዳዩን አንዱ በሌላው እያሳበቡ ማሰር በዞኑ ያለውን የፍትህ መዛባትና የአቶ ዓለማዬሁን አባባል በግልጽ የሚያሳይ ነው በማለት አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም የአቶ ዓለማዬሁ መታሰር ፖለቲካዊ አንደምታ እንዳለውና ይህም ድርጅታቸው በዞኑ ከሚያደርገው ጉልህ እንቅስቃሴና አቶ ዓለማዬሁን በማሰር ‹‹ መሪ እናሳጣለን፣ እንቅስቃሴውን እናዳክማለን ›› በሚል እንደሆነ፤ ሆኖም ይህ እንደማይሳካ፣ ይልቁንም ትግላችን በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ስለሆነ የነጻነት ትግሉን እንደሚያጠናክር በአንክሮ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም ከዚህ በፊት በኦሮሚያ ለሚደረገው የነጻነት ትግል የዞኑ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት አጋርነታቸውን መግለጻቸው በዞኑ የገዢው ፓርቲና መንግስት እንዳልተወደደላቸው፣ ካድሬዎችና ባለሥልጣናት ሁሌም እውነቱ ሲነገራቸው ከራሳቸው ጋር እየተጣሉ ለእንዲህ ዓይነቱ እርምጃ እንደሚጋበዙ ባላቸው ልምድ ላይ ተመስርተው አስረድተዋል ፡፡ ህወኃት/ኢህአዴግ የመልካም አስተዳደር ችግርንና ሙስናን ያለርህራሄ እየተዋጋሁ ነው በሚልበት ጊዜ ይህ መደረጉ በጂንካ ከተማ ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ትዝብት ላይ እንደጣለው አክለው ገልጸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃና ማብራሪያ አቶ እንዲሪስ– 0916 56 82 42