በጅማ ዝምታው ተሰበረ!!! የኦሮሞ ሕዝብ የተቃውሞ ውሎ – የዛሬው ንቅናቄ ሌሎች ብሄሮችንም ያካተተ ነበር::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በጅማ ዝምታው ተሰበረ!!! የኦሮሞ ሕዝብ የተቃውሞ ውሎ – የዛሬው ንቅናቄ ሌሎች ብሄሮችንም ያካተተ ነበር::
#Ethiopia #Oromoprotests #EthiopianOppositionparties #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ተቃውሞው ቀጥሎ ውሏል::በዚህም መሰረት በጅማ ዝምታው የተሰበረ ሲሆ በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሻቤሶንዶን ከተማ አጥለቅልቀውታል::በጉጂ ነገሌ በወለጋ ቤጊ ኤራ ቆንዳላ በሃረርጌ መቻራ በትላንትናው እለት የተገደሉትን ወገኖቻችንን በማሰብ እና ግድያውን በመቃወም ሕዝቡ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን በትላትናው እለት በመቻራ ሃረርጌ 10 ሰዎች ሲገደሉ 27 ሰዎች ቆስለዋል::የአማራ የሶማልጥ የአርጎባ የሃረሪ የጉራጌ እንዲሁም የተለያዩ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ብሄሮች በዛሬው ውሎ ለተቃውሞ የወጡ ሲሆን የዚህን ሳምንት የኦሮሞ ሕዝብ ንቅናቄ ለየት የሚያደርገው የሌሎች ብሄረሰቦችን አቅፎ መቀጠሉ ነው የወላይታ የሲዳማ እና የተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄሮችን በተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች ተቃውሞውን መቀላቀላቸው ይታወቃል::
የአግአዚ ወታደሮች እንደለመዱት በሕዝብ ላይ በመተኮስ እና በማሸበር የዋሉ ሲሆን ሕዝቡ ቆራጥነቱን በማሳየት ለውጥ ፈላጊነቱን በአደባባይ አስመስክሯል::የወያኔ ሃይሎች አሁንም የሕዝቡን ጥያቄ ተቀብሎ ከማስተናገድ እና ስልጣን ከመልቀቅ ይልቅ የሃሰት ፕሮፓጋንዳቸውን በመርጨት ላይ ይገኛሉ::በትላንትናው እለት የሞት እና የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው በርካቶች ሲሆኑ እስካሁን ከተወሰኑት ውጪ በዝርዝር የወጣ ሪፖርት የለም በናዝሪት አዳማ እና አዲስ አበባ ድረስ እንዲሁም ሃርር እና ድሬዳዋ ነቀምት ሆስፒታሎች በመታከም ላይ ሲገኙ በነገው እለትም ተቃውሞው ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል::#ምንሊክሳልሳዊ … ድል ለጭቁን ሕዝቦች!!!
