የአስገዶም ሞላ መገደል ይሁን ከነሕይወቱ መቀበር አሊያም ምንም የማይፈይዱ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳዎች ለእኛ ምንም አይጠቅሙንም::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በልማት ስም ገበሬውን ለድህነት ወጣቱን ለስደት የዳረጉ መወገዳቸው ይቀጥላል::ሕዝባዊ የእኩልነት መንግስት ይቋቋም!!! ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Freedom‬ ‪#‎Change‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) : የአስገዶም ሞላ መገደል ይሁን ከነሕይወቱ መቀበር አሊያም ምንም የማይፈይዱ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳዎች ለእኛ ምንም አይጠቅሙንም::ሕወሓት እስካልተወገደ ድረስ በኢትዮጵያ ሰላም እና እኩልነት አይገኝም::አንድ እና አንድ ጠቃሚው መንገዳችን የሕዝቦችን የትግል ንቅናቄ በመደገፍ እና በማገዝ ለፍሬ ማብቃት ነው::ወያኔ ለለውጥ ሃይል የቤት ስራ መስጠት እና አቅጣጫ እየቀያየሩ ማወዛገብ በባዶ ሜዳ ወያኔ ራስን አግዝፋ ማሳየት ልማዷ ነው::ወያኔ ደርግን ራሷ እንደጣለች አድርጋ ከፍተኛ የስነልቦና ጦርነት አድርጋ በሕዝብ ውስጥ ፍራቻ በመልቀቅ ራሷን አግዝፋ ለመኖር አሁንም ትፈልጋለች ይህቺ ጨዋታ አብቅቶላታል ሕዝብ ነቅቷል ይህቺ ምናምቴ ወያኔ ባዶነቷ ተረጋግጦ ወደ መቃብሯ እየገሰገሰች ሲሆን ሕዝብም በመቃብሯ ላይ ነጻነቱን ሊያውጅ እየተመመ ይገኛል::

በልማት ስም በተለያዩ አከባቢዎች በሕዝብ ላይ የሚሰሩ ግፎች በርክተዋል::እናለማልሃለን እንሰራልሃልን በሚል ሰበብ የሃገር ሃብት እየተዘረፈ ሕዝብ ተጠቃሚ ሳይሆን እየተበዘበዘ ገበሬዎች ከመሬታቸው ተፈናቅለው ለድህነት እና ለልመና ወጣቱ ለስደት ሴት እሕቶቻችን ለሴትኛ አዳሪነት ከመዳረጋቸውም በላይ የግፍ ጽዋ ሞልቶ ከገደቡ አልፎ ፈሷል::በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ሕዝባዊ ንቅናቄም የዚሁ አካል ሲሆን በግፍ የተማረረው ሕዝብ ጭቆና በቃኝ ብሎ ተቃውሞውን እያሰማ ሲገኝ ወያኔም በውጥረት ውስጥ እየዋዥቀች ትገኛለች::ከአንድ ብሄር የወጡ የፖለቲካ ሹምባሾች በዝምድና እና አብሮአደግነት ተሳስረው ሌላውን ሕዝብ እየበዘበዙ ይገኛሉ::በልማት ስም ዜጎች ሲገደሉ ሲታሰሩ ሲሰደዱ ሲፈናቀሉ ባለሃብት ነን የሚሉ የባለስልጣናት ዘመዶች የውጪ ዜጎች እና ግብረአበሮቻቸው በሕዝብ ንብረት እና በሃገር ሃብት ላይ ብዝበዛ ላይ ተሰማርተው ብዙሃኑን ደሃ በማድረግ ባዶ እና ትርጉም አልባ ሕይወት እንዲኖር አድርገዋል::

በኦሮሚያ ክልል በልማት እና በኢንቨስትመት ወዘተ በሚል ስም በሕዝብ ላይ የሚደረጉ ግፎች በርካታ ናቸው ይህንን ደግሞ ለማስወገድ ሕዝብ እየወሰደ የሚገኝው እርምጃ የሚደገፍ ነው::ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አገዛዙ ከሕዝብ ጫንቃ ላይ ወርዶ ሕዝባዊ የእኩልነት መንግስት እንዲቋቋም የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል::በልማት ስም ገበሬውን ለድህነት ወጣቱን ለስደት የዳረጉ መወገዳቸው ይቀጥላል::ድል ለጭቁን ሕዝቦች !!! ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.