የፌደራል ፖሊስ አድማ በታኝ አዛዥ በራሳቸው ላይ የመግደል ሙከራ አደረጉ::መትረፋቸው ያጠራጥራል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የፌደራል ፖሊስ አድማ በታኝ አዛዥ በራሳቸው ላይ የመግደል ሙከራ አደረጉ::መትረፋቸው ያጠራጥራል::
በዛሬው እለት በቃሊቲ አከባቢ በሚገኘው የፖሊስ ደህነቶች መሰብሰቢያ በተደረገው ግምገማ ላይ የፌዴራል ፖሊስ የአድማ በታኝ አዛዥ በሆነው ሻምበል የማነ መንጁስ ላይ በተደረገ ከፍተኛ ግምገማ እጅግ አደገኛ ግምገማ በመሆኑ ጫና ስለተፈጠረበት እና መቋቋም የማይችልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የያዘውን ኮልት ሽጉጥ አውጥቶ ራሱ ላይ በመተኮስ በራሱ ላይ የግድያ ሙከራ ማድረጉን በቦታው የነበሩ ምንጮች ጠቁመዋል::
ሻምበል የማነ መንጁስ ወዲያው ወደ ሕክምና የተወሰደ ቢሆንም ሁኔታው እጅግ አስጊ መሆኑን በቦታው የነበሩ ይናገራሉ::እስካሁን ከሆስፒታሉ የተገኘ መልስ ባይኖርም ኮማ ውስጥ መሆኑ ቢነገርም ምናልባት ሞቶ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት የአይን እማኞቹ አስቀምጠዋል::