በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ ቀጥሎ ውሏል::አዳዲስ ተቃውሞዎች በመጭው ሳምንት ይቀጥላሉ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

በኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ ቀጥሎ ውሏል::አዳዲስ ተቃውሞዎች በመጭው ሳምንት ይቀጥላሉ::
#Ethiopia #Oromoprotests #EPRDF #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኢትዮጵያ የኦሮሚያ የተለያዩ አከባቢዎች ተቃውሞ ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በምጥራብ አርሲ አሳሳ በምስራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ዶጉ ወረዳዎች በወለጋ በባሌ እንዲሁም በሸዋ ክፍለሃገሮች ተቃውሞ እና የመንገድ መዝጋቱ ተቃውሞዎች እንደቀሉ ይገኛሉ::በመጭው ሳምንት በተሻለ መልኩ አዳዲስ ጥያቄዎችን ያካተቱ የተቃውሞ ስልቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል:: ከፍተኛ ሃይል የሆነ የፌዴራል ፖሊስ እና የአግኣዚ መከላከያ ጦር በሻሸመኔ አቋርጦ ወደ ባሌ እየሄደ ይገኛል::
በምስራቅ ሃረርጌ የኦሕዴድ ጽ/ቤትን የተቆጣጠረው ሕዝብ በፌዴራል መንግስቱ ባንድራና በኦሕዴድ ባንድራ ምትክ የኦነግ ባንድራን ሰቅሏል::በዚሁ አከባቢ ሁለት ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸው ታውቋል::በኦሮሚያ ክልል ለሚጌዙ ሰዎች ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን በመጭው ሳምንት ከፍተኛ ተቃውሞ ይስተናገዳል ተብሎ ይጠበቃል::ወደ አምቦ እና ጉደር የሚያስገቡ መንገዶች ዙሪያቸው መዘጋቱ ታውቋል::በአምቦ የጅምላ አፈሳ እየተካሄደ መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል:: የጅማ እና ነቀምት ከተሞችን የሚያገናኘው መንገድ አርጆ ከተማ ላይ ተዘግቷል::በነጆ ከትላንትና ጀምሮ ትምህርት የተቋረጠ ሲሆን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በርካታ ዜጎች ለእስር ተዳርገዋል::#ምንሊክሳልሳዊ