የሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች በመግፋት ኣዲስ የኢሚግሬሽን ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሱዳን በኣቶ መለስ የተሰጣት መሬት ለመረከብ ሽርጉድ እያለች ትገኛለች። Amdom Gebreslasie

በ2002 ዓ/ም ሃገራቀፍ ምርጫ ወቅት ኣቶ ስዬ ኣብራሃ በኢትዮ_ሱዳን ድንበር ከ35_65 ኪ/ሜ የሚሸፍን የኢትዮጵያ ቆዳ መሬት ለሱዳን ለመስጠት ተደራድረው እንደጨረሱ ኣጋልጠው ነበር።

በዚህ መሰረት እንደ መተማ ዮውሃንስ፣ ቋራ፣ ልጉዲና ሌሎች ለም መሬቶች ለሱዳን ሊሰጡ በሁለቱ መንግስታት ዝግጅት መጠናቀቁ እየተገለፀ ነው።

በወቅቱ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ለማስረከብ ሁለቱ መንግስታት ከ17 ግዜ በላይ በድብቅ እየተደራደሩ የነበሩ ሲሆን የዚህ ድንበር ውጤትም ሱዳን በሑመራ በኩል ከነበረው ባህረሰላም የሚባለው የኢትዮጵያ ድንበር በርካታ ኪሎሜትሮች ወደ ኢትዮጵያ በመግፋት ልጉዲ በተባለው የድንበር ከተማ ኣድርገው በመትከል የሱዳን የኢሚግሬሽን ፅሕፈት ቤት ( Passports Office )ኣዲስ ህንፃ ገንብተዋል።

የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ መንግስት ለቀረበለት ገፀ በረከት ለመረከብ ከታች በምስሉ የምትመለከቱት ኣዲስ ህንፃ በልጉዲ ከተማ ገንብተዋል።

*መንግስት እነ ሃፀይ ዮውሃንስ ደማቸው ያፈሰሱበት፣ እነ ሃፀይ ቴድሮስ የተወለዱበት የኢትዮጵያ ሉኣላዊ መሬት ቆርሶ ለባእድ ኣገር መለገሱ ያቁም…!

*መንግስት ስለ በሁለቱ መንግስታት እየተካሄደ ያለው ድርድር ለህዝብ በይፋ ይግለፅ…!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO.