ረብ የለሽ ምክንያቶችን በመደርደር ህወሓትን ያርበደበደ ትግል ተቃውሞ መገኘት ምን ይባላል??? Eyasped Tesfaye


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ረብ የለሽ ምክንያቶችን በመደርደር ህወሓትን ያርበደበደ ትግል ተቃውሞ መገኘት ምን ይባላል??? Eyasped Tesfaye

በዚህ ትግል ውስጥ ባለፉት 3 ወራት ብቻ ወደ 200 የሚጠጋ ሰው በአብዛኛው ወጣቶችና ህፃናት የህይወት መስዋዕትነት ከፍለዋል
በዚህ ለ3 ወራት በዘለቀው ህዝባዊ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግ እጁን ተጠምዝዞ እቅድ ሲሰርዝ እና ሲለማመጥ ለማየት በቅተናል።
በዚህ ህዝባዊ ትግል የተነሳ እስከዛሬ በየትኛውም ድርጅት ተገኝተው የማያውቁ ዲፕሎማሲያዊ ድሎች ተገኝተዋል።
ይህ ትግል የህወሓትን እና የህወሓት ደጋፊዎችን ኢኮኖሚያዊ መሰረት አናግቷል እያናጋም ይገኛል።
~~~~~~
ድርጅቴ ተነካብኝ፣ የምወደው ሰው ተሰደበብኝ፣ ትግሉን ለምን እኔ አልመራሁትም፣ እከሌ ለምን ደምቆ ይታያል ወዘተረፈ በሚሉ ውስጣዊ ስሜት ተገፋፍቶ ረብ የለሽ ምክንያቶችን በመደርደር ይህንን ህወሓትን ያርበደበደ ትግል ተቃውሞ መገኘት ምን ይባላል???
~~~~~~~
ከዚህ ትግል በተቃራኒ የቆሙ ሰዎች
1ኛ:- የግድያው የእስራቱ እና የእንግልቱ ወላፈን በቀጥታ የማያገኛቸው ሰዎች
2ኛ:- በነሱ በኩል ካልሆነ በሌላ መንገድ የሚመጣ ለውጥን ማየት የማይፈልጉ ሰዎች
3ኛ:- ህወሓት እና ጀሌዎቹ
4ኛ:- በአማራውና በኦሮሞው መካከል ያለውን ልዩነት በማስፋት ለራሳቸው ጥቅም ማዋል የሚፈልጉ ሰዎች ቀድሞውኑም በቋፍ ላይ የነበሩና ይህን የጎንዮሽ ዘለፋ ለመጀመር አፋቸውን አሞጥሙጠው ሲጠብቁ የነበሩ
~~~~~~~
ትግሉ ሲነሳ በፌስቡክ ድጋፍ ያደረጉ ሰዎች ጥቂት ነበሩ፤ ትግሉ ሲፋፋም በፌስቡክ ላይ ደጋፊው ብዙ ሆነ…… አንድ ቁም ነገር ግን አለ:- በፌስቡክ ላይ ያለው ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ትግሉን ሲያቀዘቅዘውም ሆነ ሲያሞቀው አልታየም….. ምክንያቱም ትግሉ የአየር ላይ የሚዲያ ትግል ሳይሆን መሬት ላይ ያለ እና መሰረት የያዘ ስለሆነ። እናም እኛ እዚህ ጋር እየመጣን የምንለጥፈው ነገር የሚያተርፍልን ነገር ቢኖር ትዝብት ብቻ ነው። ትግሉ እንደሆነ ይቀጥላል።