በአቃቤ ህግ ይግባኝ የተጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማሪያን፣ በቀረበባቸው አቤቱታ ላይ ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በአቃቤ ህግ ይግባኝ የተጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማሪያን፣ በቀረበባቸው አቤቱታ ላይ ትናንት ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ቀደም ሲል አቃቤ ህግ፣ ለከፍተኛው ፍ/ቤት በተከሳሾቹ ላይ ያቀረባቸው ማስረጃዎች በአግባቡ ታይተው አልተመዘኑልኝም በሚል የጠቅላይ ፍ/ቤቱ እንደገና እንዲመለከትለት አቤቱታውን ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
በአቃቤ ህግ አቤቱታ ላይ ጦማሪያኑ ምላሽ እንዲሰጡ ፍ/ቤቱ ለትናንት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን በቀጠሮው መሰረትም ጦማሪያኑ በጠበቃቸው አማካይነት ትላንት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አቃቤ ህግ፤ በከፍተኛው ፍ/ቤት ክሱን እንዲያሻሽል በተደጋጋሚ እድል እንደተሰጠው ያስታወሱት ተከሳሾች፤ ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ የጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ ጠበቃ ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ፤ ጦማሪው በስር ፍ/ቤት በወንጀል ክስ ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ጦማሪው በሁለት ቦታ ክስ ሊቀርብበት አይገባም ብሏል፡፡
ፍ/ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለመጋቢት 20 ቀጠሮ ይዟል፡፡ ቀደም ሲል ከፍተኛው ፍ/ቤት በነፃ ያሠናበታቸውና አቃቤ ህግ ይግባኝ የጠየቀባቸው የዞን 9 ጦማሪያን ሶሊያና ሽመልስ፣ አቤል ዋበላ፣ ናትናኤል ፈለቀና ማህሌት ፋንታሁን ሲሆኑ በፍቃዱ ሃይሉ የሽብር ክሱ ወደ ወንጀል ክስ ዞሮ እንዲከራከር መወሰኑ ይታወሳል፡፡