የኦሕዴድ አባላት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መገፋትን አስመልክቶ አቤቱታ አቀረቡ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የኦሕዴድ አባላት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መገፋትን አስመልክቶ አቤቱታ አቀረቡ::
#Ethiopia #Oromoprotests #OPDO #EPRDF #MinilikSalsawi #Freedom
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በዛሬው እለት በተለይ ከኦሕዴድ ምንጮች እንዲሁም በተለያዩ ድህረገጾች እና የማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን የኦሕዴድ ከፍተኛ አመራሮች ከድርጅቱ ተገፍተዋል የሚለውን መረጃ ተከትሎ በግምገማው ላይ ያልተሳተፉ የኦሕዴድ አባላት ለኢሕኣዴግ ጽ/ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን የኦሕዴድ ምንጮች ተናግረዋል::
በአቤቱታቸው እንዳሉት የድርጅቱ አመራሮች መነሳት በኦሮሚያ ክልል ያለውን የሕዝብ ተቃውሞ የሚያበረታ ከመሆኑም በላይ አግባብ እንዳልሆነ ገልጸው ሕዝቡ የራሱን ጥያቄዎች ማሰማቱ ከመንግስት በጎ ምላሽ ማግኘት ሲገባ በሕዝብ ተመርጠዋል የተባሉ አመራሮች መግፋቱ አላግባብ መሆኑን ጠቅሰው የተገፉት አመራሮች ወደ ነበሩት ቦታ የማይመለሱ ከሆነ ድርጅቱ ለቀው እንደሚወጡ በአቤቱታቸው ገልጸዋል::በዛሬው እለት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ የቀረበው አቤቱታ እንደሚያሳየው ለችግሩ ተጠያቂ የሚሆኑት የኦሕዴድ አመራሮች ብቻ ሳይሆኑ በጉዳዩ የተሳተፉ የፌዴራል መንግስቱ የኢሕኣዴግ አመራሮችን ተገምግመው እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ሲሉ አሳስበዋል::
የኢሕኣዴግ ስራ አስፈጻሚ ጉዳዩን በዝግ አይቶት በአስቸኳይ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ የጠየቀው የኦሕደድ አባላት የአቤቱታ ደብዳቤ ችግሩ የክልሉ ብቻ ሳይሆን የፌዴራሉም ስለሆነ በሚዛናዊነት ታይቶ መፍትሄ እንደወሰድበት እና ሕዝቡም ይቅርታ ተብሎ ካሳ እንዲከፈለው ጠይቄል::ምንጮቹ እንዳሉት ብዙሃኑ የኦሕዴድ አባላት በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ የሚገኘው ግፍ እየተቃወሙ ከሕዝብ ጎን መሰለፋቸውን በገሃድ እያሳዩ ሲሆን የሕወሓት የበላይነትን በፍጹም እንደማይቀበሉት በተለያየ መልኩ ከሕዝብ ጎን በመቆም እያሳዩ መሆኑን ገልጸዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ