አምስት የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት :በርካታ ኣመራሮችና ካድሬዎች በሕወሓት ካልቾ ሊሰናበቱ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አምስት የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት :በርካታ ኣመራሮችና ካድሬዎች በሕወሓት ካልቾ ሊሰናበቱ ነው።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎OPDO‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi's photo.

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በኦሮሚያ ክፍለሃገር የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የሕወሓት ባለስልጣን የሆኑት ኣይቶ ኣባይ ጸሃዬ የኦሮሚያን ክልላዊ ምክር ቤት እንበትናለን ባሉት መሰረት በተደረገው ግምገማ የክልሉ ምክር ቤት ፕረዚዳንት እና ኣባላትን ጨምሮ የፈደራል መንግስታቸውን ባለስልጣናት እና የኦሕዴድ ኣመራሮች እንደሚያሰናበቱ እየተጠበቀ ይገኛል፤ በዚህም መሰረት ፦

፩ ኣቶ ኣባዱላ ገመዳ = የፌዴራሉ ምክር ቤት ኣፈጉባዬ(በጡረታ)
፪ ኣቶ ሙክታር ከድር = የኦሮሚያ ክ\ሃገር ኣስተዳዳሪ
፫ አቶ ለማ መገረሳ = የጨፌ ኦሮሚያ ኣፈ ጉባዬ
፬ አቶ ጣባ ደበሌ = የኦሕዴድ ስራ ኣስፈጻሚና የቢሮኃላፊ
፭ አቶ ኣቢ ኣሕመድ = የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር

እነዚህ ከላይ ስማቸው የተጠቀሱት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የኦሕዴድ ባለስልጣናት እና ኣመራሮች እንዲሁም ካድሬዎች በሕወሓት ትእዛዝ የሚሰናበቱ ሲሆን በኣንዳንዶቹ ላይ የሙስና ክስ ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬