በሐዋሳ ታቦር ትምህርት ቤት አሰቃቂ ግድያ በወያኔ ፖሊስ ተፈጸመ::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሐዋሳ ታቦር ትምህርት ቤት አሰቃቂ ግድያ በወያኔ ፖሊስ ተፈጸመ:: #Ethiopia #Hawassa

በደቡብ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ በዛረው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት በታቦር ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንድ ወጣት በፖሊስ ጥይት በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድሏል:: የወያኔ ፖሊሶች ‹‹ስለት ይዘህ ሰው አስፈራርተሀል›› በሚል በጥይት ደብድበው ገድለውታል;; ፖሊሶቹ በግፍ ከገደሉ በኋላ አስከሬኑን በድብቅ ለመቅበር ሲሞክሩ ከታቦር አከባቢ ሕዝብ ጋር ግጭት የተፈጠረ ሲሆን የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ ጣልቃ በመግባት በአስለቃሽ ጪስ በመወርወርና በመተኮስ ለተቃውሞ የወጣውን ሰው በመበተን አስክሬኑን ወስደዋል::