በወያኔ ሰራዊት ውስጥ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያበዙ ከሰራዊቱ ሊሰናበቱ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በወያኔ ሰራዊት ውስጥ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያበዙ ከሰራዊቱ ሊሰናበቱ ነው::
#Ethiopia #EthiopianArmy #Oromoprotests #EPRDF #Miniliksalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ባለፉት ቀናት የተሰበሰበው የሕወሓት የጄኔራሎች እና አማሳኝ መኮንኖች ቡድን በተለያዩ የሰራዊቱ ክፍል ውስጥ ጥያቄ የሚያበዙ እና ተቃውሞ የሚያቀርቡ የሰራዊቱ አባላት አስፈላጊው ክፍያ ተከፍሏቸው ከሰራዊቱ እንዲሰናበቱ መወሰኑን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ አሳውቀዋል::እንዲሁም በተጨማሪ ይህ መመሪያ በየክፍሉ በጥብቅ ምስጢር ከወረደ ጀምሮ ወታደሮቹ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ እንዲደረግ ተወስኗል::
በተለያዩ የሰራዊቱ ክፍል ውስጥ ጥያቄ እና ተቃውሞ የሚያበረክቱ ወታደሮች ሌላውን ሰላማዊ ወታደር እንደሚበክሉ እና ለአመጽ ለማነሳሳትም እንደማይቸግራቸው ጉዳዩን አንስተው የተወያዩት የጦር መሪዎቹ የሰራቱን ሞራል እና ታማኝነት እያላሸቁ የሚገኙት ወታደሮች እንዲሁም ለሚዲያ መረጃ ቅርብ የሆኑ የሰራዊት አባላት ሁሉ እንዲሰናበቱ ሲወሰን በከተማ ውስጥ የሚሰሩ የስርአቱ ተቃዋሚ የቢሮ የአስተዳደር ሰራተኞች በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ውስጥ በሲቭል ሰራተኝነት ተመድበው ክትትል እንዲረግባቸው መባሉም ምንጮቹ ጠቅሰው የሰራዊቱ የሞራል መላሸቅ ባሁኑ ወቅት በሕወሓት ውስጥ እጅግ አሳሳቢ አጀንዳ መሆኑን አክለው ተናግረዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ