ረሃቡ እና ድርቁ አስጨናቂና አሳሳቢ ሆኗል::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ረሃቡ እና ድርቁ አስጨናቂና አሳሳቢ ሆኗል:: ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Ethiopiafamine‬ ‪#‎FAO‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

• በድርቁ አካባቢዎች 350ሺ ተጨማሪ ህፃናት ይወለዳሉ:: — • የነፍሰ ጡር እናቶች ቁጥር እየጨመረ ነው
• የእርዳታ እህል በፍጥነት እንዲጓጓዝ ተጠየቀ:: — በድርቅ በተጐዱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ 350ሺህ ተጨማሪ ህፃናት እንደሚወለዱ የተባበሩት መንግስታት ያስታወቀ ሲሆን ለረሃቡ እና ድርቁ የሚደረገው አለማቀፍ ድጋፍ የተቀዛቀዘ መሆኑ ችግሩን አስጨናቂና በእጅጉ አሳሳቢ አድርጐታል ተብሏል፡፡

አለማቀፉ የህፃናት አድን ድርጅት በበኩሉ፤ በአሁኑ ወቅት ከሶሪያ ቀጥሎ አሠቃቂ የሰብአዊ ቀውስ ያንዣበበው በኢትዮጵያ መሆኑን ጠቁሞ፤ 4መቶ ሺህ ህፃናት የአልሚ ምግብ በእጅጉ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል፡፡
ረሃቡ እና ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ባለሙያዎቹን በመላክ ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ማድረጉን የጠቆመው የህፃናት አድን ድርጅቱ፤ በርካታ እናቶች ነፍሰ ጡር መሆናቸው አሳሳቢ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ለእናቶች እንክብካቤ ማድረግ አስቸጋሪ በሆነበት እንዲሁም እናቶች አስፈላጊውን ንጥረ ምግብ ማግኘት ባልቻሉበት ሁኔታ የነፍሰ ጡር ሴቶች ቁጥር መጨመር ችግሩን አስጨናቂ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ የሚወለዱት ህፃናት እጣ ፈንታም አሳሳቢ የህፃናት አድን ድርጅቱና የተባበሩት መንግስታት ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት ድርቁን ለመቋቋም እያደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ከ10.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ለማውጣት እንደሚገደድ የአለም የምግብ ፕሮግራም ከትናንት በስቲያ ያስታወቀ ሲሆን የገንዘብ ድጋፉም እስከ ሚያዚያ ወር ድረስ ተሰባስቦ ለተረጅዎች ድጋፍ መዋል እንዳለበት ገልጿል፡፡በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የድርቁ ሁኔታ በ1977 ዓ.ም ከተከሰተውና የ1 ሚሊዮን ገደማ ዜጐችን ህይወት ከቀጠፈው የረሃቡ እና ድርቁ ክስተት የባሰ መሆኑን የጠቆመው የአለም የምግብ ፕሮግራም፤ 10.5 ቢሊዮን ብሩን በመጪው ወር ከለጋሾች እንደሚያሰባስብም ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ለእርዳታው ያስፈልጋል ተብሎ ከተገመተው 1.4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ በአሁኑ ወቅት 37 በመቶ ያህሉ መገኘቱን የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ በበኩሉ በእርዳታ አሰጣጡ ላይ ዘይት፣ ስንዴና የማባያ የምግብ ግብአቶች በአንድነት ለተረጂዎች እየቀረቡ አለመሆኑ እርዳታ ፈላጊዎች ለእንግልት እየዳረገ መሆኑን ጠቅሶ፤ የምግብ ግብአቶች በአንድነት እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡

Minilik Salsawi's photo.