ሕዝቡ ለደርጅቶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት- ግርማ ካሳ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሕዝቡ ለደርጅቶች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት- ግርማ ካሳ
========================================
በሚቅጥሉት ሁለት፣ ሶስት ሳምንታት የተለያዩ የፖለቲካ ስብሰባዎች ይደረጋሉ። የፊታችን እሁድ ጥር 22፣ የግንቦት ሰባት አርበኞች ንቅናቄ፣ ሊቀመንበሩ ዶር ብርሃኑ ነጋ ባሉበት በዲሲ ስብሰባ ያደርጋል። “ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ” ብለዉታል።
http://ecadforum.com/…/grand-public-meeting-with-professor…/
በሳምንቱ ጥር 29 በሲያትል የማክበራቸው ምሁራን የቺካጎ ወዳጄ ዶር ጌታቸው በጋሻውና ፕሮፌሰር ህዝቄል ጋቢሳ ፣ ሃጂ ነጂብ፣ ታማኝ በየነ ፣ የግንቦት ሰባቱ አበበ ገላው….የመሳሰሉት የሚገኙበት ስብስብ ይደረጋል።
http://ethsat.com/media-jamming-mass-uprising-in-ethiopia-…/
እንደገና በሳምንቱ የካቲት 6 ፣ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራው የአዲሲቷ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ በዋሺንገትን ዲሲ ስብሰባ ያደርጋል።
http://solidaritymovement.org/…/160121-Flyer-for-SMNE-Amhar…
እነዚህ እንግዲህ ማስታወቂያቸውን ያየዃቸው ስብሰባዎች ናቸው። ሌሎች ስብሰባዎችም ሊኖሩ ይችላሉ። በቃ መሰብሰብ፣ መሰብሰብ. መሰብሰብ ..ሆኗል ስራችን።
ስብሰባ ማድረጉ፣ መነጋገሩ ባልከፋ ነበር። ግን ወቅቱ የሚጠይቀው ይሄን አይደለም። እነዚህ ደርጅቶችና ልሂቃን ከሕዝብ ጋር ከመነጋገር፣ እርስ በርስ ተነጋግረው፣ አንድ ሁሉን ያሰባሰበ ፣ የተባበረ፣ ትግሉ በቅንጅት የሚመራ ግብረኅይል መስርተው፣ ህዝብ ጋር ቢቀርቡ አይሻልም ነበርን ? በስብሰባዎቹ በአገራችን ያሉትን ችግሮች ከማውራት፣ አለም የሚያወቀዉን የወያኔዎች ሐጢያት ከመተረክን ከመተንተን፣ አናላይዝ ወይንም ኦቨር አናላይዝ ከማድረግ፣ “በሽታችን ይሄ ነው ፣ ያ ነው” ብሎ ከመጠቆም ዉጭ፣ መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ነገር ሊወጣ ይችላልን ? ለበሽታችን ፣መድሃኒትስ የሚያስገኝ ነውን ? የስብሰባዎች ጋጋታ በሜዳ ላይ የወያኔዎችን ቢሄቭየር ይለዉጠዋልን ? አይመስለኝም። እመኑኝ …. ስብሰባዎቹ ከአንድ ወር በኋላ ይረሳሉ።
አሁንም ትኩረቱ መፍትሄ ላይ መሆን እንዳለበት ነው በቀይ እስኪሪብቶ ላሰምርበት የምፈልገው። ደርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት ያላቸውን ልዩነቶች አጣበው፣ ትግሉን በጋራ ማቀናጀት ይቻል ዘንድ ፣ አንድ ሁሉን አቀፍ ግብረኅይል ለማቋቋም የሚረዳቸው፣ አንድ እንደ ጅማሬ ሊያገለግል የሚችል ፕሮፖዛል አቅርቤ ነበር።
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/50017
ፕሮፖዛሉ እንደ ዘሃበሻ፣ ሳተናው፣ ኢትዮጵያ ሪቪው/መረጃ ..ባሉ ዝነኛ ሜዲያዎች፣ እንዲሁም በሶሻል ሜዲያው፣ ለአንባቢያን ቀርቧል። ብዙ ኢትዮጵያዉይን በመርህ ደረጃ ለእቅዱ ድጋፋቸዉን ሰጥተዋል። ሆኖም የፖለቲካ ደርጅቶችና የሲቪክ ማህበራት ግን አሁንም አብሮ በመስራቱ ረገድ ትልቅ ቢሮክራሲ፣ ዘገምተኝነት እያሳዩ ነው። መቅደም ያለበትን ትተው በኋላ ሊደርስ የሚችል ነገር ላይ ሲሯሯጡ ነው የሚታዩት።
ቢይንስ በስብሰባዎቹ የምትገኙ ኢትዮጵያዉይን በዚህ ጉዳይ ድምጻችሁን እና ፍረስትሬሽናችሁን እንድትገልጹ አሳስባለሁ። ሕዝቡ መድረክ ላይ ካሉ የሚሰማበት ሳይሆን፣ መድረክ ላይ ያሉት ከሕዝቡ የሚሰሙበት ሁኔታ ነው መፈጠር ያለበት። “ከአሁን በኋላ ስብሰባ እንዳትጠሩን !!! ተባብራችሁ፣ ተስማማታችሁ፣ አንድ ሆናችሁ ካልመጣችሁ ከተሞቻችን ዝር እንዳትሉ” ብሎ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠት መቻል አለበት።