የመንግሥት ባለሥልጣናት የማስተር ፕላኑን ለመሰረዝ በወሰዱት እርምጃ በእርግጥ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን ያመለክታል? (VOA)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኢትዮጵያ፥ በኦሮሞ ተቃዋሚዎችና በመንግሥቱ የፀጥታ ኃይሎች መካከል ለሁለት ወራት ግድም ግጭቶች ከተካሄዱ በኋላ፥ ባለሥልጣናቱ የአዲስ አበባን ግዛት ለማስፋት የኦሮሞ ገበሬዎችን ያፈናቅላል የተባለውን ማስተር ፕላን መሠረዛቸውን አስታውቀዋል። ታዛቢዎች ግን፥ የመንግሥቱ ባለሥልጣናት የማስተር ፕላኑን ለመሰረዝ በወሰዱት እርምጃ ላይ ጥርጣሬ አላቸው። እርምጃው በእርግጥ የፖሊሲ ለውጥ መደረጉን ያመለክታል? ወይስ ለቀረቡበት ተቃውሞዎች ማስታገሻ ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ። ባልደረባችን ሳሌም ሰለሞን ያጠናቀረችው ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል። ያድምጡ → listen