በሃረርጌና ወለጋ ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን በኣርሲ ተማሪዎች በስለት ተወግተዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሃረርጌና ወለጋ ተቃውሞዎች የቀጠሉ ሲሆን በኣርሲ ተማሪዎች በስለት ተወግተዋል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Harerge‬ ‪#‎Wellega‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎Arsi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች አና ተማሪዎች በሕወሓት መራሹ መንግስት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ኣጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን በዛሬው እለት በወለጋ ጃርሶ አና ነቀምት እንዲሁም በሃርርጌ ጃርሶ ወረዳ ኣናኖ ሚሴ ከተማ የኣከባቢው ነዋሪዎች እና ተማሪዎች ተቃውሞ ሲያሰሙ ውለዋል።

ከዚሁ ጋር የተያያዘ ዜና በኣርሲ ዩንቨርስቲ ኣሰላ ሜዲሰን\ሕክምና ካምፓስ ከበቆጂ የመጣው ተማሪ ተስፋዬ ተሾመ የሜዲሰን ኣንደኛ ኣመት ተማሪ በሆዱ ላይ በተለያዩ ቦታዎች እንዲሁም ከጨለንቆ ሃረርጌ የመጣው የ፫ኛ ኣመት ተማሪ ከማል ኣቡበከር ኣንገቱ አና ሆዱ ላይ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ በስለት ተወግተው ተገኝተዋል።ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና አየተረዱ ይገኛሉ።

በሃገር ውስጥ አና በዓለም ኣቀፍ ደረጃ የሕወሓት ኣገዛዝ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያካሄደው ግድያ እንዲያቆም በከፍተኛ ደረጃ ተቃውሞ አየተሰማ ይገኛል።

Minilik Salsawi's photo.