ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ሊመረምር ይገባዋል ፤ ራስን መፈተሽ ለነገ ስኬት ይረዳል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ሊመረምር ይገባዋል ፤ ራስን መፈተሽ ለነገ ስኬት ይረዳል።
#Ethiopia @semayawiparty #MinilikSalsawi #Blueparty #EthiopiaOppositionparties
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ስለነጻነት እና መብት እንታገላለን በማለት የተቋቋሙ የፖለቲካ ድርጅቶች ራሳችሁን መርምሩ ….. ራሳችሁን ኣጥሩ …..ወዘተ ሲባሉ ተከባበሩ …ተመካከሩ …ተቻቻሉ ሲባሉ ……ኣመራሮቻችሁን ቀይሩ ………ወዘተ ሲባሉ ፊታቸውን ያኮስሳሉ ኣሊያን በፍረጃ ነገርን ማድበስበስ ይፈልጋሉ። እውነት ከሆኑ ማብራሪያ የሚሹ ። ሃሰት ከሆኑ ሕዝባዊ ፍትሕን የሚሹ ጉዳዮች …..
የሆኖ ሆኖ ግን በዚህ ሰሞን ብቻ ሰማያዊ ፓርቲ ላይ ያነጣጠሩ ሁለት ዘገባዎች ኣንብበናል። እነዚህ ዘገባዎች ደሞ የሰማያዊ ኣመራሮችን ስም ጠቅሰው ማስረጃ ኣለን ደብዳቤ በጃችን ይዘናል የሚሉ ዘገባዎች መሆናቸው ሁለት ጉዳይችን እንዳይ ኣስገደደኝ ኣንድ የሰማያዊ ፓርቲ ጋዜጦቹ አንደሚሉት እውነት ከሆነ ራሱን ሊፈትሽ ሁለት ደግሞ ውሸት ከሆነ “ፍትሕ ባይገኝም” በሕግ ፊት ጋዜጦችን በመገተር ድርጅቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጥበት ይገባል።

ኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ም፨ቤት፣ በገንዘብ ምዝበራና በአሰራር ግድፈት የጠረጠራቸው አምስት ከፍተኛ አመራሮች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስ አድማስ ምንጮች ገለፁ ሲል የፓርቲው ዲሲፕሊን ኮሚቴን ጠቅሶ በጃንዋሪ 2/2016 ዘገባ ( http://www.addisadmassnews.com/index.php… ) ማውጣቱን ይታወሳል። ይህ ጋዜጣ የፓርቲ ኣመራሮችን ስም እየጠቀሰ የሰራውን ዘገባ ፓርቲው ሕገወጥ ነው በማለት ከመቃወም ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ሲያስተባብል ከርሟል።ሰማያዊ ፓርቲ በህዝብ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ለማረጋገጥ ሲል አንዲህ ኣይነት ዘገባዎችን ዝም ብሎ ማለፍ የለበትም።የጋዜጣአ ተነባቢነት ሰፊ አስከሆነ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲን ተስፋ ያደረጉ ሕዝቦች ጥያቅዐ ምልክት ውስጥ ፓርቲውን ያስገቡታል ታማኝነትም ይቀንሳል፥ፓርቲው ኣዲስ ኣድማስን በይፋ ሊቃወመው ይገባል ኣሊያም ሊያርመው ካልሆነም ዘገባው መሰረት ኣድርጎ እውነታውን መናገር ግዴታ ኣለበት፥ካልሆነ ችግሩ አየተለጠጠ ነገ ኣዲስ ነገር ይወልዳል።
የኣዲስ ኣድማስ ጋዜጣ ቀለሙ ሳይደርቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ሰማያዊ ፓርቲ ኣራት ኣባሎቹን ጥላቻ በማስፋፋት በሚል ማባረሩን ነገረን ( http://www.ethiopianreporter.com/…/%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B…) ኣሁንም ምንጭ የተባለው የዲሲፒሊን ኮሚቴው ሲሆን ይባስ በዲሲፒሊን ኮሚቴው ሃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ በሚል ማስረጃውን ኣጠናክሮ ይናገራል ሪፖርተር ኣማርኛው። ኣያይዞም ከፓርቲው ቀድሞ ራሱን ያሰናበተው አና በእስር ላይ የሚገኘውን አቶ ዮናታን በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የታሪክና የጎሳ ጥላቻ ያላቸው ቅስቀሳዎችን በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የአገሪቱን ቀደምት መንግሥታት ታሪኮች ያጎደፈ፣ ለጥላቻ የሚያነሳሳ፣ በሕዝብ መካከል የባህል መከባበር እንዳይኖር የጥላቻ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ፓርቲው በውሳኔው አስታውቋል፡፡ ሌሎቹም የተሰናበቱት አባላት ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸውን በማብራራት ከፓርቲው መሰናበታቸውን ገልጿል፡፡
ሁለቱም ጋዜጦች ማስረጃ ኣድርገው ያቀረቡት የፓርቲውን የዲሲፕሊን ኮሚቴን ነው።ጋዜጦቹ የፓሪውን ሰዎች ስም ጠቅሰው ስለፓርቲው የውስጥ ጉዳይ ኣደባባይ ኣውጥተዋል ይህ ደግሞ ካለምክንያት የፓርቲው ገበና ኣልባከነም፤ በፓርቲው ከፍተና ኣመራሮች እና በዲሲፒሊን ኮሚቴው መካከል ኣለመግባባቶች እንዳሉ ፍንጭ ያሳያል።ተጨማሪ ተባረሩ የተባሉ ኣባላት በዲሲፕሊን ኮሚቴው ሃላፊ ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የታሪክና የጎሳ ጥላቻ ያላቸው ቅስቀሳዎችን በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የአገሪቱን ቀደምት መንግሥታት ታሪኮች ያጎደፈ፣ ለጥላቻ የሚያነሳሳ፣ በሕዝብ መካከል የባህል መከባበር እንዳይኖር የጥላቻ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ፓርቲው በውሳኔው አስታውቋል፡፡ማለት ፓርቲው ያለተዘዋዋሪ በቀጥታ ሕወሓት ኣስሮ በሚያሰቃያቸው ታጋዮች ላይ ምስክርነት መስጠቱ አና ሕወሓት ለሚያቀርበው ሃሰተኛ ክስ ማጠናከሪያ መሆኑ መዘንጋት የለብንም በሌላ ኣነጋገር ፓርቲው ኣባሎቹ በኣስተሳሰብ ስለተለዩ ብቻ ለሕወሓት የሃሰት ክሶች ኣሳልፎ በመስጠት ተባባሪ ሆኗል ማለት ነው፥በመጨረሻ ማለት የምፈልገው ፓርቲው በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ ማብራሪያ ሊሰጥ አና ጋዝጦቹን ሊከስ ይገባዋል፥ፍሕ ሕ ባይገኝም ሕዝቡን በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳል፥አውነት ከሆነም ፓርቲው ሰማያዊ ፓርቲ ራሱን ሊመረምር ይገባዋል ፤ ራስን መፈተሽ ለነገ ስኬሕ ይረዳል። #ምንሊክሳልሳዊ