ሰማያዊ ፓርቲ ኣባሎቹን ጥላቻን የሚሰብኩ በማለት በመወንጀል ለሕወሓት አገዛዝ ኣሳልፎ ሰጠ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ሰማያዊ ፓርቲ ኣባሎቹን ጥላቻን የሚሰብኩ በማለት በመወንጀል ለሕወሓት አገዛዝ ኣሳልፎ ሰጠ።

በመጀመሪያ ለማለት የምንፈልገው ሪፖርተር ጋዜጣ የሃሰት መረጃ ካስተላለፈ ሰማያዊ ፓርቲ በሕግ ሊጠይቀው ይገባል፥ በመቀጠል በዘገባው መሰረት የሪፖርተር ጋዜጣ ኣማርኛ አትም ባወጣው ዜና የሰማያዊ ፓርቲ ኣራት ኣባላቱን በመወንጀል ሕወሓት ባቀረበባቸው ክስ ላይ ቤንዚን መጨሩ ታወቀ። የሰማያዊ ፓርቲን የብሔራዊ ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ኃላፊ ሃና ዋለልኝ ፊርማ የተላለፈው ውሳኔን ጠቅሶ ጋዜጣው እንዳለው ቀደም ብለው በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ከፓርቲው ማግለላቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ያስታወቁትን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊውን አቶ ዮናታን ተስፋዬን ጨምሮ፣የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑትን አቶ እያስፔድ ተስፋዬን፣ አቶ ጋሻዬነህ ላቀና አቶ ዮናስ ከድርን የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ተላልፈው በመገኘታቸው፣ ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከፓርቲው እንዲወገዱ ማድረጉን ገልጿል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ኃላፊ ሃና ዋለልኝ ፊርማ የተላለፈው ውሳኔ እንደሚያስረዳው፣ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ ፬፪(፭) ሥር ከባድ የሥነ ሥርዓት ቅጣት ስለሚያስከትሉ ጥፋቶች ተደንግጓል፡፡ የፓርቲውን ዓላማ፣ ፕሮግራምና ፖሊሲ መፃረር አይቻልም፡፡ በመሆኑም የተጠቀሱት አባላት ደንቡን በመተላለፋቸው ቅጣቱ እንደተላለፈባቸው አስታውቋል፡፡

አቶ ዮናታን በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ የታሪክና የጎሳ ጥላቻ ያላቸው ቅስቀሳዎችን በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና የተለያዩ የአገሪቱን ቀደምት መንግሥታት ታሪኮች ያጎደፈ፣ ለጥላቻ የሚያነሳሳ፣ በሕዝብ መካከል የባህል መከባበር እንዳይኖር የጥላቻ ቅስቀሳ ማድረጋቸውን ፓርቲው በውሳኔው አስታውቋል፡፡ ሌሎቹም የተሰናበቱት አባላት ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸውን በማብራራት ከፓርቲው መሰናበታቸውን ገልጿል፡፡ጋዜጣው ጽፋል።