የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም እየሰሩ ሕዝብን መወንጀል ኣጥብቀን አናወግዛለን።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም እየሰሩ ሕዝብን መወንጀል ኣጥብቀን አናወግዛለን።
#Ethiopia #Ethiomuslims #EBC #EPRDF #Justice #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ልማት እና ኣሸባሪ እያሉ ማጭበርበር እንደተነቃበት እና በዚህ ዘመን እንደማይሰራ ወያኔ ሊያውቀው ይገባል፤ ህዝብ ነቅቷል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ እንጂ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም አልናፈቀንም። ላለፉት ኣራት ኣመታት ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱ እና ወኪሎቻቸው አንዲፈቱ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በጽናት ሰላማዊ ትግላቸውን በማድረግ ከዚህ ደርሰዋል፤ ኣሁንም ከትግሉ ሳያፈገፍጉ በጋራ በመሆን መብታቸውን አና የሃይማኖት ነጻነታቸውን ለማስከበር ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በትግል ላይ ይገኛሉ፥ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ለመወንጀል በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ የቴሌቭዥን ዶክመንተሪዎች በሃሰት ከመፈብረክ ጀምሮ ስድብ እስር እና ግድያ የተለያዩ ክሶች በካንጋሮ ፍርድ ቤት ቢቀርብባቸውም በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት እና ተዓማኒነት በማጣቱ ኣገዛዙ በራሱ ብቻውን ሃይሉን በመጠቀም ፕሮፓጋንዳውን ወደራሱ አያስተጋባው ይገኛል፤ውሸት ሲደጋገም ውነት ይሆንልኛል የሚለው ኣገዛዙ ሰሚ ጆሮ ሳያገኝ መቃብሩ ላይ ደርሷል።
የወያኔ ኣገዛዝ የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ማሽን የሆነው ኢቢሲ የፊታችን ቅዳሜ ዳግም ዶክመንታሪ ፊልም በሚለው የቅዥት ህልም ኢትዪጲያዊያን ሙስሊሞችን አስፈሪ አድርጎ የሚስልበትን ዶክመንታሪ ሊያሳይ ነው፡፡ ውዱን አቡበክርን እና የጥላቻ ፈረስ ጋላቢ የሆነውን ሰላሃዲን ወዚር በማስታወቂያ ላይ ታይቷል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ለመተንኮስ ከሚደረጉ ጥረቶች ኣንዱ ነው።የወያኔ ኣገዛዝ ኣልገባዉም እንጂ ሙስሊሙ ሕዝብ በፍቅር በትእግስት በጋራ መኖር በሰላም የታነጸ ጽኑ አና ጥብቅ ሕዝብ ነው ስለዚህ የወያኔ ዶክመንተሪ ቅዥት አንደማይሳካ ካሁኑ ልንነግረው እንፈልጋለን። ልማት እና ኣሸባሪ እያሉ ማጭበርበር እንደተነቃበት እና በዚህ ዘመን እንደማይሰራ ወያኔ ሊያውቀው ይገባል፤ ህዝብ ነቅቷል።መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍትሕ እንጂ የሃሰት ዶክመንተሪ ፊልም አልናፈቀንም። ዛሬም እንደ ትላንቱ የጎንዪሽ የርስበርስ ትንኮሳን ለማነሳሳት የሚጥሩትን በዝምታ ሊቀጣቸው ሁሉም ዝግጁ ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኣንድነታቸውን በማጥበቅ ከምንም በላይ በጽናት ትግላቸውን የሚቀጥሉ ሲሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከሙስሊም ወገኖቹ ጎን በጽናት እንደሚቆም በተደጋጋሚ እንዳሳየው ሁሉ ኣሁንም ከትግሉ ጎን እንደሚቆም ለማረጋገጥ እወዳለሁ። ትግላችን እስከ ደል ደጃፎች ይቀጥላል!!! ድል ለመላው ኢትዮጵያውያን!!! #ምንሊክሳልሳዊ
