ሃሮማያ – ተማሪዎች ላይ ሲተኩሱ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች ከገበሬዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ኣደረጉ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ሃሮማያ – ተማሪዎች ላይ ሲተኩሱ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች ከገበሬዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ኣደረጉ።
#Ethiopia #Oromoprotests #Harerge #MinilikSalsawi #EPRDF
በዛሬው እለት በሃረርጌ በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ አየተደረገ ሲገኝ የሃሮማያ ዩንቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በኣግዓዚ ወታደሮች ታፍሰው ወደማይታውቅ ስፍራ ተውስደዋል። በሃረርጌ ሃሮማያ ጭሮ ቆቦ ክራ መኢሶ እና ኣከባቢው በከፍተኛ ደረጃ ተማሪው ገበሬው አና የከተማው ነዋሪ በመሰባሰብ ተቃውሞ አያሰሙ ይገኛሉ።
ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የሃሮማያ ወጣቶች ወደ ዩንቨርስቲው በመሰባሰብ ለተማሪዎች ያላቸውን ኣጋርነት ኣሳይተዋል። በሃሮማያ ቴክኖ ካምፓስ የመጀመሪያ ኣመት ተማሪ የተገደለ ሲሆን ስሙም ፋሂም ኣብዱላዚዝ ሲባል የጨለንቆ ኣከባቢ ተወላጅ ነው፤የቴክኖ ካምፓስ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው አየወጡ ይገኛሉ።ከሃሮማያ የሚወጡ ተማሪዎች ላይ ሲተኩሱ የነበሩ የሕወሓት ወታደሮች ከገበሬዎች ጋር በመጋጨታቸው የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል::
