በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ኣከባቢዎች ተቃውሞው አንደቀጠለ ነው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ኣከባቢዎች ተቃውሞው አንደቀጠለ ነው::
#Ethiopia #Oromoprotests #EPRDF #MinilikSalsawi #Change
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – በወዲወላቡ አና በጅማ ዩንቨርስቲዎች አንዲሁም በሃረርጌ ክፍለሃገር መኢሶ በድዐሳ ዲካቻ አና በተለያዩ ዞኖች የገጠሩ አና የከተማው ሕዝብ በመደባለው በከፍተኛ ደረጃ ተቃውሞውን ካለማቋረጥ አየገለጸ ይገኛል።የጂማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለሊቱን በሙሉ የተቃውሞ መፈክር ሲያሰሙ አምሽተዋል። አሁን በደረሰን ቪዲዮ መሰረት ተማሪዎቹ የንጹሀንን ዜጎችን ደም ያፈሰሱና የግድያ ትእዛዝ የሰጡ ባለስልጣናት ሁሉ በአስቸኳይ ለፍርድ ካልቀረቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደማይመለሱ ገልጸዋል።
በሃሮማያ ዩንቨርስቲ ለሊቱን በተፈጠረ ችግር የሕወሓት ትጣቂዎች ፫ ተማሪዎችን መግደላቸው ሲጠቆም በወዲ ወላቡ ዲያቆን ሳሙዔል የተባለ ከድሬዳዋ ለትምህርት የሄደ በጩቤ ተወግቶ መሞቱ ተነግሯል።
ወንድማችን ዲያቆን ሳሙኤል ከተማ በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአምስተኛ አመት የምህንድስና ተማሪ ነበር በዚህ ኣመት በከፍተኛ ማእረግ ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል፣ ሳሚ የድሬዳዋ ልጅ ገንደቦዬ ነዋሪ የደብረምህረት ቅ/ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ተማሪ እና አገልጋይ ነው፡፡ የተገደለው በሕወሓት ቅጥረኛ የኦሕዴድ ካድሬ ተማሪዎች በዽምጽ ኣልባ መሳሪያ በጩቤ ተወግቶ ነው። ይህ ግድያ የተፈጸመው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጋራ አንዳይታገል በዘር ከፋፍሎ ለማፋጀት በሕወሓት የተጠነሰሰ ሴራ ነው።
በጅማ ዩንቨርስቲ በተማሪዎች አና በሕወሓት ወታደሮች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰባት ተማሪዎች ቆስለዋል።በሃሮማያ ዩንቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን በወዲወላቡ ፪ ተማሪዎች ሞተዋል።በሸዋ ሰላሌም አንዲሁ ተቃውሞ መሰማቱ ታውቋል።በሃረርጌ በደሳ ወጣቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ በመኢሶ አንዲሁ ተቃውሞ ተሰምቷል።
