እውን ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል ? ??


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


እውን ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌ የሞት ፍርድ ተፈጽሞበታል ? ?? Minilik Salsawi
ይህ የሕወሓቶች መሽረፈት ነው የሚሉት ኣንድ የዲፕሎማቲክ ደህንነት ቢሮ ሰው ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌ በምእራባውያን ዲፕሎማቶች ጫና አና ክትትል የተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አና በየሳምንቱን በኣባቱ በኣቶ ጽጌ አንደሚጎበኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፥ ተቃዋሚዎች ከሚደነባበሩበት የግምት ፖለቲካ መላቀቅ አና በመረጃ መጠንከር ኣለባቸው ይላሉ የዲፕሎማቲክ ደህንነቱ። ከዚህ የተሻለ መረጃ ኣለኝ የሚል ካለ ያካፍለን።
በኦሮሚያ ክልል ያለው ሕዝባዊ ትግል ኣትኩሮቱን ለማዞር የሚደረጉ ወከባዊ መረጃዎችን በጥንቃቄ ልንመለከት ይገባል፥፥ወያኔ ከገባበት ኣጣብቂኝ መውጣት ባቃተው ሰኣት ላይ ታጋይ ኣንዳርጋቸው ላይ ይህን አርምጃ ይወስዳል ብሎ ማሰብ ከፖለቲካ ሚዛን ኣኳያ ኣያስኬድም የሚል እምነት ኣለኝ፤፤ኣትኩሮታችን ሁሉ ሕዝባዊ ትግሎችን በኣንድነት በማጠናከር በጋራ ተጋግዘን የወያኔን ኣምባገነን መንግስት ልንደመስ ስ ይገባል።