የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት (ኦህዲኅ) የትግል አጋርነት መግለጫ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ቀን 29/04/2008 ዓ/ም ==== የትግል አጋርነት መግለጫ —-
የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ኦህዲኅ/የዞን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና አባላት በዛሬው ቀን በመሰባሰብ ለ8 ሳምንታት በኦሮሚያ እና በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የአዲስ አበባና አጎራባች የኦሮሚያ አካባቢዎች የጋራ ማስተር ፕላን ምክንያት በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞ ከሚያሰሙ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ጎን(አጋር)መሆናችንን እያረጋገጥን የተወሰደባቸውን እጅግ አሰቃቂ አምባገነናዊ እርምጃ በጽኑ እንቃወማለን!
ድንበራችንን አሳልፎ ለመስጠት የሚደረገውን ከህዝብ የተደበቀ ስምምነትና ለማስፈጸም የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንዲሁም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ለመብት፣ፍትህና ነጻነት የሚደረጉትን ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ለማፈን እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ እንቃወማለን፣ ከሚደረጉት ሰላማዊ የዜግነት መብታችንና ክብራችን ለማስመለስ፣ ሉዓላዊነታችንን ለማስከበር ለሚደረጉ ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች አጋርነታችንን እንገልጻለን፡፡
በዚህ አምባገነን የህወኃት ጠባቂ አጋዚ ጥይት ለነፃነታችን ለወደቁት፣ለቆሰሉ፣በግፈኛው እስር ቤት ለተወረወሩ እና ትግሉን ግብ ለማድረስ በቁርጠኝነት ለተጋፈጡ ጀግኖቻችን ታላቅ አክብሮት እንዳለንና የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ስርአት ተላቆ የሀገሩና የነፃነቱ ባለቤት እስከሚሆን ሰላማዊ ትግላችንን የበለጠ አንድ ሁነን እንደምንቀጥል እናረጋግጣለን!
ነፃ ለመዉጣት እንተባበር !!!
የኦህዲኅ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
29/04/2008
ጂንካ