አስደሳች ዜና – የኢትዮጵያ ፊደላት በላፕቶፕ እና በደስክቶፕ ተቀረፁ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Fikre Tolossa — አስደሳች ዜና – የኢትዮጵያ ፊደላት በላፕቶፕ እና በደስክቶፕ ተቀረፁ
ማን አንዲህ ዐይነት ቁምነገር ፈፀመ ወይም አስፈፀመ ቢባል ወይዘሮ ገነት አየለ ናት። አስዋም ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ቴሌሺዥን የአንግሊዝኛ ቁዋንቁዋ አስተናጋጅ፥ በሁዋላ ደግሞ የቤዛ ጋዜጣና የመጀመሪያው የሴቶች መፅሄት አዘጋጅ የነበረችው፥ እንዲሁም ከማንም ቀድማ ኮረኔል መንግሥቱ ኅይለማርያምን ቃለመጠይቅ አድርጋ “የኮሎኔል መንግሥቱ ትዝታ” በሚል ርዕስ መፅሃፍ የሳተመችው ግንባር ቀደም ሴት ናት። አሁንም አንደልማድዋ ግንባር ቀድማ ፊደሎቻችንን አቃላልን አንደ ሌላው የዐለም ሰዎች በ ላፕቶፕ እና ደስክቶፕ ላይ አስቀረፀችልን። የአንግሊዝኛ ሆሄያት abcd ሳንመታ በቀጥታ የኢትዮጵያዎቹን ፊደላት ከመምታታችን በተጨማሪ አንድን ፊደል ሁለቴ ሳንመታ አንዴ ብቻ በመጨቆን ተደጋጋሚ የሆኑትን ፊደሎቻችንን ልንከትባቸው እንችላለን ማለት ነው። በዚህም መሰረት አያሌ ነገሮችን በቀላሉ መፃፍ አንችላለን። እንግዲህ የኢትይጵያ ቁዋንቁዋዎች እና ስነፅሁፎች አለፈላቸው ማለት ነው። እኛም አንደሌላው ህዝብ ለወግ በቃን። ወይዘሮ ገነትን እንኩዋን ደስ አለሸ አንበላት። ለዝርዝር መረጃ የሚከተለውን የዌብሳይት አድራሻዋን ተጭናችሁ የፈፀመችውን እፁብ ድንቅ ሥራ እዩላት። እኔ ክማንም ተሽቀዳድሜ ልገዛ ቆርጬ ነበር። ዳሩ ግን አሜሪካ ገና አልደረሰም አለችኝ። ለጊዝው የሚሸጠው አውሮፓና ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ዌብሳይቱ አነሆ። like ብንልላት ደስ ሳይላት የሚቀር አይመስለኝም። የወለደውን ሲስሙለት እንደሚባለው።