ጥቂት የሀገሬን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ሳስባቸው – (መልካምሰላም ሞላ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ጥቂት የሀገሬን ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ሳስባቸው –Melkam-selam Molla
እንደ ሸንበቆ ከፍ ብለው ይታዩን ተስፋ ስናደርግባቸው ፍሬያቸው ገለባ ይሆናል። ተስፋ የጣሉባቸው በበኩላቸው ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ፡ ከስራቸው እየተፈናቀሉ ፡ እየታሰሩ ፡ እየተደበደቡ እየተሰቃዩ ፍዳቸውን ሲበሉ ጥቂቶች ስልጣን የጠማቸው ቢሮ ቁጭ ብለው መግለጫ እየሰጡ፤እንዴት እኔ ታዋቂ አልሆንኩም እነርሱ ማን ስለሆኑ በሚል ተንኮል በራቸውን ዘግተው ሴራ ሲጎነጉኑ ያድሩና ሲነጋ የራሳቸውን ቡድን መስርተው መናከስ ይጀምራሉ ። አንድ ማንኪያ መርዝ አንድ በርሚል ውሃ እንደሚበክል ሁሉ ጥቂቶችም አንድም የወያኔ ተልዕኮ አስፈፃሚ በመሆን ተቃዋሚ መስለው በመግባት አልያም ለስልጣን ካላቸው ፅኑ ፍላጎት የተነሳ የአብዛኛው መስዋዕትነት እና ትግል ላይ እንቅፋት ሆነው ህዝቡ በአማራጭ ፖርቲዎች እምነት እንዲያጣ ያደርጉታል ። እነዛ በሞራል ተነሳስተው መከራቸውን ያዩትም ተስፋ ይቆርጣሉ። ዳር ሆነው መበታተኑን በጉጉት ለሚጠብቁት ፌሽታ ይሆናል ። ግዴለም ይስተካከላሉ ብለው የእዮብን ትዕግስት ለተዋሱ ደግሞ ፖርቲው አደጋ ላይ ነው እናድነው ብለው ሲቀሰቅሱ ይሰነብቱና ከቻሉ ”ፊት መሪ” ቦታውን ይዘው ለመጉዋዝ ይጥራሉ። ካልቻሉ ዋናውን አዳክመው አዲሱን ማንነታቸውን ይዘው ለመምጣት ልክ መስለው ለመታየት ከጣሩ በሁዋላ ጥቂት አኩርፈው የወጡትን ጨምረው በአዲስ ማልያ ይከሰታሉ።
የመጠላለፍ ፖለቲካ ላልገባው ሀገር ወዳድ የሀገር ፍቅር ብቻውን በፖርቲ ውስጥ ታቅፎ ለመታገል ምክንያት ሊሆነው አይችልም ። ትልቁን አዞ ለመግደል ባህር ውስጥ ገብቶ አሳዎች ቦጫጭረው ይገድሉታል። ሩቅ አልሞ በድፍረት ተጋድሎ ሲመጣ ውጭ አጨብጭበውለት በጀግንነት ወደ ቤቱ ሲመለስ ከወሮበላው መንግስት ይልቅ ልክ ከእንቅልፉ እንደሚባንን ሰው ጭብጨባው የሚረብሻቸው ውስጥ ያሉት ናቸው ። የጭቃ እሾህ ሆነዋል ። ማንነታቸው ይታወቃል ግን አይታዩም ።የሚገለጡት ሲወጉ ብቻ ነው ።
ብዙ ጊዜ ኢህአዴግ ባንዳች ተአምር ቢወርድ ሀገሪቷን ማን ይመራታል??? ብለን ተወያይተን እናውቃለን። በተለያዩ ጊዜ ብቅ ብለው ተስፋ ባሳዩን ውስጣችን ብርሀን ፈንጥቆ ሳይጨርስ እርስ በርስ ተጠላልፈው ይወድቃሉ ። የሚገርመ አንድም በተልዕኮ አንድም ስልጣን ጥማት ወይም የደገፈውን አካል ምኞት ለማሳካት ከውጭ ላለው አካል ስራ የሚያቀሉሉት ውስጥ ያሉት ናቸው ።
የቤታቸው ጉዳይ ተቻችለው አልፈው ወጣ ሲሉ ደግሞ፤ ከጎረቤታቸው ጋር ለአንድ አላማ በተለያየ ጎራ ተሰልፈው እርስ በርሳቸው ሲነካከሱ ዋናውን ይተውታል። ለዛም ነው ለመዋሃድ ከሚያመሳላቸው ይልቅ የሚያለያያቸውን ምክንያት የሚደረድሩት ። ተባብረው አላማቸውን ከማሳካት ይልቅ ከውህደታቸው በሁዋላ ማን ፕሬዚዳንት ሊሆን ? የሚለው ስለሚያስጨንቃቸው ስለአንድነት ይሰብካሉ ግን አንድ አይሆኑም ።
ድርጅት ውስጥ ታቅፎ ለመታገል በውስጥ ያለውን አሻጥር ተቁዋቁሞ ሲያልፍ ጎረቤቱ የእሱን ውድቀት ሌት ተቀን በጉጉት ይጠብቃል።
በመጠላለፍ የተሞላ የፖለቲካችን መድረክ ለወያኔ እድሜ እንዲሰጠው አድርጎታል ። ብርቱዎች በጥቂት ሆዳሞች ተሰናክለው ሲቀሩ እንደማየት ምን የሚደብር ነገር አለ። ጀግኖች ጥንካሬ ከአባቶቻቸው ወርሰው ጨለማን ለመግፈፍ ሲሰሩ ጥቂት ግን ለትንሽ ጊዜም ይሁን በእውነት ተቀብተው ዝነኛ ለመሆን ከአርአያዎቻቸው ክፋት እና ተንኮል ወርሰው ይቅበዘበዛሉ ፦ህዝብ አንቅሮ እስኪተፋቸው ድረስ
እናንተ ለህዝባችሁ ስትሉ መከራን የተሸከማችሁት ፅናቱን ይስጣችሁ