የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ የተድበደቡ ተማሪዎች በወህኒ ቤት እየሞቱ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ የተድበደቡ ተማሪዎች በወህኒ ቤት እየሞቱ ነው

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተቃውሞ ተከትሎ ብዙሺህዎች በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ለእስር መዳረጋቸው አይዘነጋም ። በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች የሚገኙበት ሁኔታ አለመታወቁና ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ባለመደረጋቸው ቤተሰቦች ጭንቀት ውስጥ ናቸው ።እስረኞቹ በታፈሱበት ወቅት ድብደባ የተፈፀመባቸው በመሆኑም በህይወት መቆየት መቻላቸው ብዙዎችን ለስጋት ዳርጓል።በአንዳንድ የማጎሪያ ካምፖችም ለሞት የተዳረጉ መኖራቸው እየተሰማ ነው ።በወለጋዋ ላሎ ቂሌ ነዋሪ የነበረው የሁለት ልጆች አባት መሰረት ዲንቃ በተፈፀመበት ድብደባ በሚገኝበት ወህኒ ቤት ህይወቱ አልፏል።ከወሊሶና ከወለጋ ዩኒቨርስቲ ታፍሰው ከተወሰዱ ተማሪዎች መካከልም በወህኒ ቤት የሞቱ መኖራቸው እየተሰማ ነው