አሳስሮ አስገድሎ አሰድዶ ጩኸት ከዛ ዝም … ግን ዝምታችን እስከመቼ ነው::ተቃዋሚ ሃይሎች ራሳችንን እንፈትሽ:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ስለዚህ አንዱና ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድክመት ስር ነቀል የለውጥ የፖለቲካ ስትራቴጂ አማራጭ ሐሳብ፣ አማራጭ ፕሮግራምና አማራጭ ስትራቴጂ አለመከተላቸው ነው፡፡ ሁለተኛው ድክመታቸው አማራጭ አደረጃጀትና የእንቅስቃሴ ጥንካሬ አለማሳየታቸው ነው፡፡ ለመሆኑ ተቃዋሚ ድርጅቶች አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ምን ያህል ይሆናሉ? ድንገት ካልሆነ ለመሆኑ ዓመታዊ ጉባዔ ያካሂዳሉ ወይ? ለመሆኑ በፓርቲያቸው ውስጥ ወቅቱን የጠበቀ ምርጫና ግምገማ ይካሄዳል ወይ? የውስጥ ኦዲት ይደረጋል ወይ? ግልጽነት አለ ወይ? ፓርቲውን ሁሌም የሚመራው አንድ ዓይነት ኃይል ነው? አባላት ይሁኑ የለውጥ ሃይል አክቲቭኢስቶች ከታሰሩ በኋላ ምን ጠንካራ እርምጃ ይውሰዳል? በቂ የሆነ የደህነት እና የስለላ መዋቅር አላቸው ወይ ? ወዘተ የሚለው መታየት አለበት፡፡ሌላው ትልቁ ድክመት ይህ ነው፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በውስጣቸው ጥንካሬ አይታይም፡፡ ዲሞክራሲያዊ ሕይወት አይንፀባረቅም፡፡ ይህ የሚያሳየን አማራጭ ሐሳብ መኖሩ ብቻ ሳይሆን፣ አማራጭ ሐሳብ ተይዞም ወደ ድርጅታዊ እንቅስቃሴና ጥንካሬ ካልተቀየረ በተስፈኛ ሚዲያዎች በሲዲና በወረቀት በፕሮፓጋንዳ ብቻ ማሳየት አቅም አለመኖሩን ማሳያ ነው፡፡
በአጠቃላይ ሲታይ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆንና ጥንካሬ ሲባል ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲጠናከሩ ያስፈልጋል፡፡ በኢትዮጵያ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ባለመኖሩ ጉዳት እየደረሰ ነው፡፡ በኢሕአዴግ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን በግራም በቀኝም ሲያይ ጠንካራ ተቃዋሚ ስለማያገኝ፣ ኢሕአዴግን የሚተካ ኃይል ይኖራል ብሎ መተማመን አልቻለም፡፡ ምን ተቃዋሚ አለና እያለ ተስፋ እየቆረጠ ነው፡፡ በመሆኑም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሌላ ወገን ሳያሳብቡ መጀመሪያ ውስጣቸውን ይፈትሹ፤ ድክመታቸውን ይመኑ፡፡ ብቁ ተቃዋሚ ለመሆን ይጣሩ፡፡ ድክመታቸው ሲነገራቸው ለጥንካሬያቸው ስለሚበጅ በእጅጉ ያስቡበት፡፡ የብቁ ተቃዋሚ የጥበብ መጀመሪያም አማራጭ ሐሳብና አማራጭ ጥንካሬ ያለው ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጣ የፖለቲካ ስትራቴጂ እስከ መስዋትነት መከተል ነው፡፡አሳስሮ አስገድሎ አሰድዶ ጩኸት ከዛ ዝም … ግን ዝምታችን እስከመቼ ነው::ራሳችንን እንፈትሽ:: #ምንሊክሳልሳዊ