የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶችና የሶሻል ሚዲያ አክቲቪስቶችን በጅምላ ማፈስ ተጀመረ!!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi – በተለያዩ ቦታዎች (ኦፌኮ) እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ አባላቶች የእስር ትህዛዝ ተላልፎ እየታደኑ መሆኑ አሁን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በን/ስ/ላ/ወረዳ06 ቄራ ጎፋ ማዞሪያ በሶሻል ሚዲያ እንዲሁም በአካባቢብ በድፍረት መንግስትን በመተቸት የሚታወቀው ወጣት ታጠቅሸዋ ኃ/መስቀል(ጎራው) ተብሎ የሚታወቀው በፖሊስ ቤቱ ተከቦ ተይዟል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ፖሊስ አካባቢውን በመውረር ብርበራ እየተደረገ ነው፡፡ ወጣት ታጠቅሸዋ ኃ/መስቀል በተለያዩ ሰልፎችና ቅስቀሳዎች ያለምንም መሸማቀቅ ተሳትፎ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በሶሻል ሚዲየ መንግስትን የሚተች ጠንካራ የለውጥ ሀይል ነው፡፡

ማዕከላዊ በእስር ላይ የሚገኙ

1. ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው
2. ቴዎድሮስ አስፋው፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት
3. ዳንኤል ተስፋየ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት  ከፍርድቤት ታፍኖ ተወስዷል
4. ኤርሚያስ ጸጋየ፣ የሰማያዊ አባል
5. ፍሬው ተክሌ፣ የሰማያዊ አባል… ናቸው።

ከእነዚህ መካከል ፍሬው ተክሌ፣ ቴዎድሮስ አስፋው እና ኤርሚያው ጸጋየ በተያዙበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ምንጮች ገልጸዋል።