መድረክ እና ሰማያዊ ያሰቡት ሰላማዊ ሠልፍ ዕውቅና መስጠት መቸገሩን የአዲስ አበባ ከንቲባ ድ/ቤት አስታውቋል፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) እና ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሑድ ታኅሳስ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ለማድረግ ያሰቡት ሰላማዊ ሠልፍ እንደማይካሄድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ በመድረክ አማካይነት የዕውቅና ጥያቄ የቀረበለት ሰላማዊ ሠልፍ፣ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተፈጠረው ሁከት በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ግድያና የኃይል ተግባር ለማውገዝ ነው፡፡ አስተዳደሩ ግን ሰላማዊ ሠልፉ የሚካሄድበት ከራስ መኮንን ድልድይ እስከ ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት መናፈሻ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ) የትራፊክ መጨናነቅ የሚበዛበት፣ ትላልቅ የመንግሥት ተቋማትና በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስለሚገኙበት ለሰላማዊ ሠልፉ ዕውቅና መስጠት መቸገሩን አስታውቋል፡፡