ዛሬም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸው መሆናቸውን እየተናገሩ ነው – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
አንድ የአሰላ ከተማ ነዋሪ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ የአንደኛ፣ የሁለተኛና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ሠላማዊ ሠልፍ ወጥተው የአዲስ አበባን የአካባቢዋን ከተሞች የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላንና ኦሮሚያ ውስጥ ይካሄዳል ያሉትን እሥራትና ግድያ መቃወማቸውን ገልፀዋል፡፡
አንዲት የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ከሰልፉ ወቅት ስትሮጥ ሽቦ ላይ ወድቃ የአንድ ዐይኗን ብርሃን ለማጣት መዳረጓን የከተማይቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ አንድ የከተማይቱ ነዋሪ ደግሞ ሆዷ ላይ በዱላ ተመትታ በብርቱ መጎዳቷን አመልክተው ትምህርት ተቋርጦ ከተማይቱ በጦር እየተጠበቀች ነው ብለዋል፡፡ ዝርዝር ዘገባውን ያዳምጡ ↓