ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ላወጁት የተሳሳተ ትምህርት መልስ በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በተለየየ ጊዜ በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ቀስፈው የያዙ ችግሮችን በጥልቀት በመመርመር ከቤተክርስቲያኒቷ ዶግማና ቀኖና አኳያ በመገምገም ከነመፍትሄያቸው በበርካታ ርዕሶች መጣጥፎችን ማቅረባቸው ይታሳል። በቅርቡም የተሃድሶ እምነት አራማጆች ከ 2000 ዓመታት በላይ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስትተላለፍና ሁልቆ መሳፍርት የሌላቸው ካህናትና ምዕመናን የተጋደሉላትን ኃይማኖች ለመበረዝ፣ ለመቀየጥና ለማጥፋት የረቀቀና የተለያየ ፈርጅ ያለው እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆናቸው ይታወቃል። ለዚህም አንዱ መንስዔ የዘመናችን አንዳንድ ካህናት ሳይማሩና ሳያውቁ ማዕረጉንና መጠሪያውን ብቻ ይዘው ካህናት ነን እያሉ አውደ ምሕረት ላይ እየቆሙ ምዕመናንን ወደ ገደል እየመሩ የሚገኙ ቀላል ቁጥር ያላቸው አይደሉም። እነዚህ ካህናት የቤተክርስቲያናችንን ቋንቋ የሆነውንና ምትክና አማራጭ የሌለውን ግዕዝን አጥርተው ስለማያውቁና ሚስጥሩ ስለማይገባቸው እራሳቸው ተሳስተው ምዕመናንንም ወደ አዘቅት ይዘው እየነጎዱ ነው። ለእነዚህ ዓይነት ዕውቀት ለጎደላቸው ካህናት ትምህርት እንዲሆናቸውና ከጥፋታቸው እንዲመለሱ በማሰብ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ በግዕዝ ቋንቋ አዘጋጅተው 12 ገጾችን የያዘ ጦማር አቅርበዋል። ይህንን ጦማር ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ለተሐድሶ እምነት አዋጅ መልስ