የትግራይ ህዝብ ውርደት :- 1.2 ሚ. ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚጠበቅ -1.5ሚ. ሰርቶ ለምግብ በድምሩ 2.7 ሚልዮን ህዝብ ጥገኛ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የትግራይ ህዝብ ውርደት = Amdom Gebreslasie

************

በኣሁኑ ሰዓት በድርቅ ምክንያት 1.2 ሚልዮን ህዝብ ኣስቸኳይ እርዳታ የሚጠባበቅ ሲሆን 1.5 ደግሞ በሴፍትኔት እርዳታ( ሰርቶ ለምግብ) በድምሩ 2.7 ሚልዮን ህዝብ ጥገኛ ሆኖ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል ኣደጋ መከላከልና ዝግጁነት ፅህፈት ቤት ሰነዶች ይገልፃሉ። ኣቶ ልጃለም መተባሉ ባለ ስልጣንም ገልፀዋል።

ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሳይቀሩ “የትግራይ ገበሬ 100% ሞዴል ነው” ብለው እንዲናገሩ ያስገደዱት የትግራይ ባለስልጣናት ባለፈው ዓመት ዘመነ ምርት 38 ከክረምት ኣዝመራ፣ 75 ሚልዮን ኩንታል እህል ከመስኖ ልማት እንዳመረቱ የገለፁበት ውሸት በውርደት ላይ ውርደት ተከናንበው እንዲያርፉ ኣድርጓቸዋል።

ህወሓት በ25 የስልጣን ዘመኑ 2.7 ሚልዮን የትግራይ ህዝብ ከውጭ በሚመጣ የእርዳታ እህል ጥገኛ እንዲሆን ኣድርጓል።

የመለስ ራኢ ትሩፋት 2.7 ሚልዮን ህዝብ በቀጥታም በተዘዋዋሪም የእርዳታ እህል እንዲጠብቅ ማድረግ ነው።
ይሄ እውነታ ለህዝባችን ትልቅ ውርደት ነው። በገሃዱ ዓለም ይህ ሆኖ ሳለ “ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ኣንድ ናቸው” የሚል መፎክር ይዘው ሌተቀን ይጮሃሉ።
የሚገርመው የህወሓት ጭሆት ደግመው የሚያስተጋቡ የዋህ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞችም በርካቶች መሆናቸው ነው።

‪#‎ETHIOPIAN_FAMINE‬

‪#‎ክፉ_ቀን‬

‪#‎ዘበን_ኣካሒዳ‬

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

it is so.

Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.