በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የተነሱ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለዋል::የፖለቲካ ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ ይገኛሉ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች የተነሱ ተቃውሞዎች ዛሬም ቀጥለዋል::የፖለቲካ ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ ይገኛሉ:: #Ethiopia #Oromoprotests #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከታታይ ካለማቋረጥ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተነሳው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የመልካም አስተዳደር የፍትህ እና የለውጥ ጥያቄዎችን አካቶ በስፋት የቀጠለ ሲሆን በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞችም ሕዝቡ በዛሬው እለት ድምጹን ማሰማቱን ቀጥሏል:: እንዲሁም በቡራዩ ከተማ እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ ተከትሉ ሁለት የኦሮሚኛ ዘፋኞች ቢሊሱማ ድንቁ እና ጂረና ሺፈራው በሕወሓት ፖሊስ መታፈናቸው ሲታወቅ የአልጀዚራ ጋዜጠኞች አቶ በቀለ ገርባ እና የኦሮሞ ገበሬዎችን ቃለመጠይቅ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከኢትዮጵያ ተባረዋል::
በዛሬው እለት ለሶስተኛ ጊዜ በሃሮማያ በወለጋ ላሎቃሌ በደንቢ ዶሎ በመንዲ በአየራ ወለጋ በአርሲ አሰላ ፕሪፓራቶሪ ት/ቤት አሰላ ሜዲካል ኮሌጅ ሸዋ መቲ ከተማ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆ በሌሎች ቀሪ ከተሞችን ሕዝቡ አድባባይ ለመውጣት እና ድምጹን ለማሰማት እየተዘጋጀ ይገኛል የወያኔ ወታደሮች በየአከባቢው የኦሮሞ ነጋዴዎችን የሃገር ሽማግሌዎችን እና ተሰሚነት ያላቸውን ሰዎች እየነጠሉ በጥይት መምታት መጀመራቸውን አንዳንድ ዘገባዎች ይጠቁማሉ::እንዲሁም በኦሮሚያ ዙሪያ በየአከባቢው የተመደቡ ባለስልጣናት እና ሹሞች ቤተሰቦቻቸውን በተመደበላቸው ላንድ ክሩዘር ይዘው ወደ አዲስ አበባ በመሸሽ ላይ ይገኛሉ:: #ምንሊክሳልሳዊ