የኦሮሚያ ከተሞች፤ የተቃውሞው ሰልፎችና ሌሎች ያልተጠበቁ አደጋዎች ሥጋት – VOA
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
“…እስካሁን ድረስ በሰላም (ኦሮምያ ውስጥ) አብረን የኖርን ሰዎች አማራውም፥ ትግሬውም፥ ወላይታውም ሆነ ሁሉም የሚያጋጨን ምንም የለም። ጥያቄው የጋራ ነው። የምሄደው ለዲሞክራሲና ለነጻነታችን ነው።… የእርስ በእርስ ግጭት ለሃገርም ለወገንም (የሚያመጣው) ምንም ጥቅም የለም። ጥያቄውንም አይመልስም።” አቶ በቀለ ነጋ፥ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግሬስ ዋና ጸሃፊ።
“አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ፤ በእነኚህ ጉዳዮች ላይ፥ በዓላማው ላይ፥ በይዘቱ ላይ፥ የተሟላ ግልጽነት፥ የተሟላ መተማመን፥ የተሟላ የጋራ መግባባት ባልተያዘበት ሁኔታ እነዚህ ጥያቄዎች እየተነሱ እያሉ የክልሉ መንግስት አይቶ እንዳላየ ሆኖ ዘሎ ወደ አፈጻጸሙ የሚገባበት ሁኔታ አይኖርም። ይሄንን ለሕብረተሰቡ ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።” የኦሮምያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር።
በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎችና አንዳንድ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች መሰንበቻውን በተከታታይ በማካሄድ ላይ ያሏቸው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አሁንም ቀጥለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ “የክልሉ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሰሞኑን የሰጧቸው የቴሌቭዥን መግለጫዎችና አስተያየቶች ለችግሩ ሁነኛ ምላሽ የሰጡ አይደሉም፤” ሲሉ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው በአካባቢዎቹ የሚንቀሳቀሰው የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግሬስ ይተቻል።
በርዕሱ ላይ የተጠናከሩትን ዘገባዎች ከዚህ ያድምጡ፤