ፍርሃት የለቀቀበት ወያኔ በአሰላ የሚደረገውን የአትሌቲክስ አመታዊ ውድድር ማምሻውን ሰረዘው::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ፍርሃት የለቀቀበት ወያኔ በአሰላ የሚደረገውን የአትሌቲክስ አመታዊ ውድድር ማምሻውን ሰረዘው::
#Ethiopia #OromoProtests #EPRDF #AddisAbabaMasterPlan #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi : የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በሸዋ ወለጋ ሃረርጌ ባሌ ጅማ እና በተለያዩ ከተሞች እና ወረዳዎች የሕዝቡን የለውጥ እና የነጻነት ንቅናቄ በመፍራት የወያኔ አገዛዝ ስፖርትን በጎሳ ከፍሎ በየአመቱ የሚያከብረው የኦሮሚያ የአትሌቲክስ ሻምፒዮንሺፕ ውድድር የመክፈቻው ስነስርዓት ነገ ታህሳስ 4 2008 በአሰላ የነበረ ቢሆንም መሰረዙ ታውቋል::ይህ ውድድር እንዲሰረዝ የተደረገው ከሰአታት በፊት ሲሆን ተወዳዳሪዎች አሰላ ገብተው ልምምድ ላይ መሆናቸው ሲታወቅ በየመጡበት እንዲመለሱ ትእዛዝ ተላልፏል::
በሕዝብ ተቃውሞ እየተናጠ የሚገኘው አገዛዙ የሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ጸረ ሕዝብ እና ጸረ ሰላም መሆናቸውን እያወቀ ሊያቆም ባልመቻሉ ተቃውሞዎች ወጥለው አስተዳደሮችን እስከማስወገድ ደርሰዋል::የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞየመልካም አስተዳደር እና የፍትህን የመብትና የነጻነትን ጥያቄ እንደወለዱ የኦሮሞ ልጆች በተግባር ባሳዩት ሕዝብ በጋራ በመራው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰው በአገዛዙ ጥይት ባልተበገረው ሰልፍ አይተናል::
አመታዊ የአትሌቲክስ ውድድሩ ወደ ተቃውሞ ይቀየራል በሚል ስጋት እንዲሰረዝ የተደረገ መሆኑን የገለጸው ምንጩ ውድድሩ ቢካሄድ ኖሮ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን እና የኦሮሞ ተማሪዎችን ግድያ በመቃወም በጥቁር ልብሶች እና በመፈክሮች ሊታጀብ ነው የሚሉ መረጃዎች ለአገዛዙ መድረሳቸው ተጠቁሟል:: #ምንሊክሳልሳዊ