በሰሜን ጎንደር መተማና የሱዳን ቦርደር ጋላባት መንገድ ተዘጋ ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።

በሰሜን ጎንደር መተማና የሱዳን ቦርደር ጋላባት መንገድ ሙሉ ለሙሉ እንደተዘጋ ከስፋራው የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል። ከሱዳን ፖርት ወደብ ነዳጅን ጨመሮ ወደ ኢትዮጵያ በተለይም ለጎንደርና ለትግራይ የሚገባው በመተማ በኩል እንደሆነ ይታወቃል።
በጎንደር ወልቃይት ጠገዴ፣ በአርማጭሆ በተለያዩ ጊዜያት ችግሮች እንደሚከሰቱ ይታወቃል። በተለይም በወልቃይት ጠገዴ የሚኖረው ሕዝብ “ወደ ትግራይ ክልል የተቀላቀልነው በኃይል ነው። እኛ ጎደሬዎች ነን” በሚል ጥያቄዎች እየቀረቡ ነው።