ወያኔ ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት ቀረጻ አካሄደ::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ወያኔ ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት ቀረጻ አካሄደ::
#Ethiopia #EthioMuslims #Anwarmosqueexplosion #AnwarConspiracy
የወያኔ መንግስት በዛሬው እለት አንዋር መስጅድ ና በህገ-ወጡ መጅሊስ ለተጨማሪ ፕሮፖጋንዳ ቀረጻ አካሄደ
የመንግስት ሚዲያዎች ለትናንቱ የአንዋር መስጅድ ፍንዳታ ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በዛሬው እለት የአንዋር መስጅድ ኢማም ጡሃ ሃሩን እና የአንዋር መስጅድ አስተዳደርን አቶ ሸምሱን እንዲሁም የአንዋር ምእምናን በማለት የተዘጋጁ ካድሬዎችን አነጋገሩ::
”መውሊድ ማክበራችንን እንቀጥላለን በአሸባሪ ጥቃት መውሊድ ማክበር አንተውም ” የአንዋር መስጅዱ ኢማም – ”ጁምአን ጠብቀው ሆን ብለው ነው አሸባሪዎች ጥቃት የፈጸሙት ‘የአንዋር አስተዳደር አቶ ሸምሱ
ጥቃቱ አክራሪነትን ከመታገል አይገታንም የህገወጡ አዲስአበባ መጅሊስ መጅሊስ አመራር ዶክተር አህመድ
ትላንት ቢቢኤን ጨምሮ ለተለያዩ ሚዲያዎች ኢንተርቪው አልሰጥም ያሉት ሚዲያዎች በዛሬው እለት ለመንግስት ሚዲያ አስገራሚ ንግግሮችን አድረገዋል
ቢቢኤን ታህሳስ 1/2008
በትላንትናው እለት በታላቁ አንዋር መስጅድ ከጁምአ ሶላት በሁላ የቦንብ ፍንዳታ መከሰቱን ቢቢኤን በቀዳሚነት ከዚያም በመንግስት ሚዲያዎች፤ እንዲሁም በውጭ ሚዲያ አልጀዚራ እና ቢቢሲን ጨምሮ ክስተቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
በርካታቶችም ድርጊቱ በመንግስት የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በኦሮሚያ የተነሳበትን ከባድ ተቃውሞ ለማስቀየስ እና ሙስሊሙን በመውሊድ ሰበብ ለመከፋፈል የታቀደ መሆኑ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡
የዚህ ማሳያ የሚሆኑ ቀረጻዎች በዛሬው እለት ኢዜአ በታላቁ አንዋር መስጅድ ጠዋት 3፡30 በመገኘት የአንዋር መስጅድ አስተዳደር አቶ ሸምሱን እና ኢማሙን ጡሃ ሃሩን አነጋግረዋል
በትላንትናው እለት ስለሁኔታው እንዲያስረዱ በተደጋጋሚ ከቢቢኤን ሲደውላላቸው ሶላት ላይ ነኝ እናንተ ጋር ሶላት የለም ወይ ሲሉ የነበሩት አቶ ሸምሱ ዛሬ ለኢዜአ ሲናገሩ እንደነበር በቦታው የነበሩ እማኞች ገልጸዋል
አቶ ሸምሱም ለኢዜአ ሲናገሩ አደጋው ሆን ተብሎ ጁምአን ጠብቆ የተፈጸመ መሆኑን በመግለጽ ጁምአ በመሆኑ አንዋር ግቢ ውስጥ መኪኖች ፓርኪንግ ስለማይቆሙንጅ መኪኖች ቢኖሩ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ መንግስት እነዚህን አሸባሪዎች ፈልጎ ይቅጣልን ሲሉ በተማጽኖ እና በማስተዛዘን ተናግረዋል
የአንዋር መስጅዱ ኢማም ደግሞ ለኢቲቪ ዛሬ ሲቀረጹ ሲናገሩ ” የፈለጉትን ቢያደርጉ መውሊድ ማክበራችንን እንቀጥላለን በአሸባሪ ጥቃት መውሊድ ማክበር አንተውም ” በማለት የተጠበቀ ከፋፋይ ንግግራቸውን እና የመንግስትን እኩይ የመከፋፈል ግልጽ አላማ የተገመተውን ተናግረዋል፡፡
የአንዋር መስጅዱነ ኢማም ጡሃ ሃሩን ከዚህ በፊት በአንዋር መስጅድ ስለገቡት የፕሮቴስታን ሰባኪያን አያገባኝም ምን አገባችሁ ሲኩ ቆይተው አሁን ደግሞ ሆን ተብሎ በመውሊድ ለሚያከብሩ ተብሎ የተደረገ የሽብር ጥቃት በማስመሰል የመንግስት ጉዳይ አስጻሚ መሆናቸውን በሚያስብቅ መልኩ ተናግረዋል፡፡
ከሁለቱ በተጨማሪም አንዳንድ የአንዋር መስጅድ ምእምናን በማለት ሶስት የተዘጋጁ ምልምል ካድሬዎችን ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታው ለማዋል ቃለመጠይቅ አድረገዋል ይህንንም በቦታው ላይ የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ይህንንም በምሽት ዜና ወይም በቀጣይ በሚሰራ የሃሰት ዶክመንታሪ ሊታይ ይችላል ተብሏል፡፡
በትላንትናው እለት የተፈጠረው አደጋ ሆን ብሎ መንግስት ከዚህ ቀደም በአሜሪካ መንግስት እና በዊክሊክስ እንደተጋለጠው ራሱ አደጋ በማድረስ አሸባሪዎች አደረሱት በማለት ይሰራው የነበረው ድራማ አካል መሆኑን በርካቶች እየተናገሩ ነው፡፡
በሌላ በኩል የህገወጡ የመጅሊስ አመራሮችም ጥቃቱ ከጀመርነው የአክራሪነት ትግል አይገታም ሲሉ ለህዋሀት ልሳን ለሆነው ፋና ተናግረዋል መንግስት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በአክራሪነት እና አሸባሪነት በመፈረጅ በቀጣይ ጊዜ ለሚያደርገው ጥቃት ድራማ ነው ተብሏል
በአሁኑ ሰአት መንግስት ባለበት ከፍተኛ ተቃውሞ ምክኒያት አለም አቀፍ ሽብረተኝነት ስእል ለማላበስ እና ለማስቀየስ የሰራው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ማህበረሰቡም የመንግስትን እና የደህንነቶቹን እኩይ ሴራ እየተከታተለ በህብረት ማክሸፍ እንዳለበት ድምጻችን ይሰማ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡
