ወሊሶ አንድ የስምንት አመት ልጅ ጨምሮ ስምንት ሰዎች ተገደሉ:: የለውጥ ጥያቄው ቀጥሏል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) = በወሊሶ ከተማ ተማሪው ገበሬው እና አጠቃላይ ነዋሪው ለለውጥ ባነሳው ተቃውሞ አንድ የስምንት አመት ልጅን ጨምሮ 8 ሰዎች መገደላቸውን የወሊሶ ነዋሪዎች ተናግረዋል::ከትላንትና ጀምሮ ብወሊሶ በተደረገው ተቃውሞ በከተማው ያለውን አስተዳደር ከማፍረስ ጀምሮ እስከ እስር ቤት ሰብሮ በግፍ የታሰሩ ንጹሃንን እስከማስለቀቅ ድረስ የተሳካ ስራ በሕዝቡ ተሰርቷል::ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን የአጋዚ ወታደሮችን የጫኑ ሰባት ከባድ መኪናዎች ወደ ቦታው ቢያመሩም በህዝቡ በተወሰደው የመንገድ መዝጋት እና የተቃውሞ መበርታት ወደ ከተማው መግባት አልቻሉም::
ይህ የሕዝብ ብሶት የወለደው ተቃውሞ ማንም የፖለቲካ ድርጅት ያልወልደው መሆኑ ሕዝቡ በጋራ እና በአንድነት ቆሞ በማሳየት ሃያልነቱን አስመስክሮበታል::ሕዝቡ ለአምባገነን እንደማይተኛ በተግባር አሳይቷል::በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያደርሱ መንገዶች መዘጋታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን አለመከፈታቸው ታውቋል::ተማሪዎችና አርሶ አደሮች ወደ ከተሞች የሚወስዱትን ዋና ዋና መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮችና ግንዶች ዘጋግተዋል። የፌደራል ፖሊሶችና የወያኔ አጋዚ ቅልብ ወታደሮች እንደልባቸው ለመንቀሳቀስ ተቸግረዋል:: #ምንሊክሳልሳዊ
