ተማሪዎች ዛሬም ቁጣቸውን ሲገልጹ ውለዋል:: በሙልካጡሪ ሕዝቡ ከመሃል ሃገር ወደ ሰሜን ክፍለሃገራት የሚወስደው መንገድ ዘግቶት ይገኛል::
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
በሸዋ በባሌ በሃረርጌ እና በወለጋ ክፍለሃገራት ተማሪዎች ዛሬም ቁጣቸውን ሲገልጹ ውለዋል::

#Ethiopia #OromoProtests #AddisAbabaMasterPlan #MinilikSalsawi
በሙልካጡሪ ሕዝቡ ከመሃል ሃገር ወደ ሰሜን ክፍለሃገራት የሚወስደው መንገድ ዘግቶት ይገኛል::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከፎቶግራፎቹ እንደምንመለከተው የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን የሚቃወሙ የኦሮሞ ተማሪዎች እንዲሁም የአከባቢው ሕዝብ በሰሜን እና ምስራቅ ሸዋ በባሌ አጋርፋ በሃረርጌ ቀርሳ በወለጋ , በኢንጪኒ በወያኔ ጥይት መስእዋት በሆነው በበቀለ ሰቦቃ ይቀብር ስነስርዓት ላይ በአዋሳ ዩንቨርስቲ በሻምቡ ሆሮ ጉድሩ በእጄሬ አጋርፋ እና አርሲ ነገሌ በጀልዱ እና ሲሲሪ ተቅውሞዎች የነበሩ ሲሆን በሙልካጡሪ ሕዝቡ ከመሃል ሃገር ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ክፍለሃገራት ጎንደር የሚወስደው መንገድ ዘግቶት ይገኛል::
አለማያ ዩንቨርስቲ ሃረር ካምፓስ – በአጋርፋ ባሌ – በጪሊያ – በጉዶ – በአምቦ እንዲሁም በአዳማ ናዝሬት እና በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞው አገርሽቶ ሕዝቦች ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ:: Minilik Salsawi



