በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል እና በወታደራዊ እዞች እንዲሁም በደህንነት ቢሮ ያለው መረጃ …


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል እና በወታደራዊ እዞች እንዲሁም በደህንነት ቢሮ ያለው መረጃ …
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎AddisAbabaMasterPlan‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኦሕዴድ ባለስልጣናት ላይ ቁጥጥሩ ጠንክሯል::የየወረዳ ጸጥታ ሃላፊዎች ወደ ፌዴራል ደህንነት ቢሮ የተጠሩ ሲሆን በምትካቸው ከፌዴራል ፖሊስ የተመረጡ የሕወሓት መኮንኖች ከነጋሻ ጃግሬዎቻቸው በየቦታው ተልከዋል::ከፍተና ወታደራዊ ጄኔራሎች በየካምፑ ውስጥ ያሉ ታማኝ ወታደሮች እና ወታደራዊ ደህነቶች በተጠንቀቅ እና በንቃት በካምፑ የሚገኙትን የሁለት ብሄር ተወላጆች እንዲጠብቁ መመሪያ ተሰቷቸዋል::አዲስ አበባ ካሳንቺስ እና አሮጌ አይሮፕላን ማረፊያ ባሉ የደህነት ቢሮዎች በሁለት ቡድን የተከፈለ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል::

በየክፍለሃገሩ የሚገኙ የኦፌኮ አመራሮች እና አባላት ላይ ጠንከር ያለ ክትትል እየተደረገ ይገኛል::ከደህነት ቢሮ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ያለውን የተቃውሞ አደጋ የሚቆታጠር ቡድን የተቋቋመ ሲሆን ከሕወሓት ባለስልጣን ስልኮች በስተቀር የብኣዴን የኦሕድድ እና የደሕአዴግ ባለስልጣናት የስልክ ግንኙነቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየውን ጨምሮ በደህንነት እይታ ስር ናቸው::ችግሩ በቁጥጥር ስር እደዋለ ምንም ችግር እንዳሌለ እና ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ቢሞከርም እንዲሁም የተቃውሞው ስሪት ወያኔ ነው የሚል ፕሮፓጋንዳ ለማስነዛት ቢሞከርም ስርዓቱ አደጋ ውስጥ እንዳለ የባለስልጣናቱ እና ጭፍሮቻቸው ከላይ ታች ሩጫ ይናገራል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬