አዲስ አበባን የማስፋት ኢትዮጵያን የማጥበብ አላማው ጥቅሙ ለሕወሕቶች ብቻ ነው:: (እንዴት?) (ምንሊክ ሳልሳዊ)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


አዲስ አበባን የማስፋት ኢትዮጵያን የማጥበብ አላማው ጥቅሙ ለሕወሕቶች ብቻ ነው:: (እንዴት?)
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎AddisAbabaMasterplan‬ ‪#‎Ethiosudanborder‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕወሓት አገዛዙን በእጁ ካደረገ ጀምሮ ለሃገርም ይሁን ለሕዝብ የፈየደው ምንም ነገር የለም::በልማት ስም እየሰራን ነው በሚል ሃሰተኛ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ ሃገሪቷን ለእዳ ሕዝብንም ለድህነት ከመዳረግ ውጪ አንድም የተሰራ ስራ የለም::ተሰርቷል የሚባለውም ስራ ቢኖር አለም አቀፍ ደረጃ እና ጥራቱን ያልጠበቀ ለፖለቲካ ፍጆታ የተሰራ የጥቂቶችን ኪስ በሙስና ያደለበ ለመሆኑ በገሃድ የታየ ጉዳይ ነው:: ጋምቤላ ላይ በብሄረሰቦች ስም እየተጨፈረ ሌላው የኢትዮጵያ አካል ላይ ደግሞ መብትህ ተከብሯል የተባለው የሚነገድበት ሕዝብ ደሙ ደመከልብ እየተደረገ እየተገደለ ይገኛል::አሁንም የአዲስ አበባ መስፋት እና የኢትዮጵያ መጥበብ ዋና አላማው እና ግቡ የሕወሓቶችን እና የጋሻ ጃግሬዎቻቸውን ኪስ ለማደለም የታቀደ እንጂ ለሕዝብ የታሰበ አይደለም::

ከአዲስ አበባ መስፋት ብንጀምር ሕወሓት በወይዘሮ አዜብ መስፍን እና በደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራ እጅግ ግዙፍ የሪያል ስቴት የአግሮ ኢንዱስትሪ ካምፓኒ የተለያዩ ፋብሪካዎችና የአበባ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻዎችን ከቱርክ እና ኢምሬትስ ባለሃብቶች ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ገበሬዎችን በማይረባ ካሳ በማፈናቀል ሃገርን ለመበዝበዝ እና ሕዝብን ለመጨቆን የታሰበ እቅድ እንደሆነ የታወቀ ጉዳይ ነው::ኦሕዴድን ሰንጎ የያዘውን እና አብዛኛው አባሎቹ የማይደግፉት ይህ የማፈናቀል እቅድ ከኢሕኣዴግ አባሎች ከሕወሓት ውጪ ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠመው ሲሆን እንዲሁም ከተቃዋሚ ፓርቲ አቶ በቀለ ገርባ ይህን ማስተር ፕላን አስመልክተው እንዳሉት እኛ ማስተር ፕላኑን የማንቀበለው በትክክል የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የተዘጋጀ ነው የሚል እምነት ስለሌለን ነው፡፡ መንግሥት በዚህ አሳቦ ወደ ኦሮሚያ አጎራባች ከተሞች ዘልቆ እየገባ ለባለስልጣናትና ለስርአቱ አገልጋዮች ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ፣ የሀብት መዝረፊያ፣ በህዝብ ላይ ደግሞ ሌላ የጭቆና ቀንበር መጫኛ፤ ማንነቱን፣ ቋንቋውን፣ ባህሉን የማጥፋት ዘመቻ ነው ብለን ነው የምንወስደው በማለት በግልጽ አስቀመጠውታል::የአዲስ አበባ መስፋት ዋናው አላማ ለባለስልጣናትና ለስርአቱ አገልጋዮች ተጨማሪ ገቢ ማስገኛ፣ የሀብት መዝረፊያ፣ በህዝብ ላይ ደግሞ ሌላ የጭቆና ቀንበር መጫኛ ነው::ይህ ደግሞ ገበሬውን ለለማኝነት እና ለስደት ቤተሰቡን ለመበተን እና ለረሃብ ስለሚዳርገው አጥብቀን መቃወም አለብን::

የኢትዮጵያን መጥበብ ደግሞ ለጥቀን ስናየው ሃገራችን በምእራብ በኩል ከሱዳን ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የዲማርኬሽን/ድንበር የማስመር ስራ በሚል ሰበብ ከ1200ኪሎ ሜትር በላይ ከኢትዮጵያ መሬት ተውስዶ ለሱዳን እንደሚሰጥ እና የሚገርመው ደሞ የኢትዮጵያውያንን ቅርሶች ያካተቱ እንዲሁም አጼ ቴዎድሮስ ዳግማዊ የተማሩበት ገዳም ሳይቀር ለሱዳን ተላልፎ ለመስጠት እየተደገሰ ይገኛል::ይህ የድንበር ማካለል ስራ በተመለከተ ሱዳን ኢሕኣዴግን በማመስገን በማሞገስ ላይ ትገናለች የወያኔ አገዛዝም ያሌለ ታሪክ እና ያልተጻፈ መረጃ በሃሰት በመጥቀስ እውነት አድርጎ ለማቅረብ እየሞከረ ስለሚገኝ ይህንንም አጥብቀን ልንቃወመው ይገባል:: በአጠቃላይ ሁለቱ የአገር ጉዳይ ነው እጅግ አንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነ በጋር ልንቆም እና በጋራ ልንቃወም ይገባል::መፈራረጁ እና አቃቂር ማውጣቱ ለጊዜው አቁሞ የጋራ የሃገርና የሕዝብ ጠላትን በጋራ ልንዋጋ ይገባል::ማወቅ ያለብን ጉዳይ ቢኖር አዲስ አበባን የማስፋት ኢትዮጵያን የማጥበብ አላማው ጥቅሙ ለሕወሕቶች ብቻ ነው::ለሃገር እና ለወገን ጥቅም የማይሰጠውን እቅድ ሁሉ ልንቃወም ይገባል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.