ድሃው የትግራይ ገበሬ ( ኄኖክ የሺጥላ )
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
የ-ማስታወቂያ አላማ አዲስ ነገርን ለብዙ ዘመን የምታውቀው ፣ የምታውቀውን ደሞ አዲስ አስመስሎ ማቅረብ ነው ይላል አንዱ ፈረንጅ ፣ በራሱ በፈረንጁ ቋንቋ አባባሉ እንዲህ ተጽፎ ነበር ( Advertisement is making the new familiar and the familiar new )። አዎ አንዳንድ የፖለቲካ ትንታኔዎች ማስታወቂያ ነው የሚመስሉኝ ። የምናውቀውን አዲስ አዲሱን ደሞ ልክ የምናውቀው አድርገው ሲያቀርቡ ሳይ ።
ዛሬ ትንሽ ስለ ድሃው የትግራይ ገበሬ እናውራ ። በመጀመሪያ ድኃ የሚለው ሁኔታን ዓመልካች ቅጥያ የትግራይ ገበሬ ከሚለው ቀድሞ ሲመጣ ትንሽ ሆድ የምያባባ ነገር እንዳለው እንገንዘብ ። ድሃው የሚለውን አውጥቼ <የትግራይ ገበሬ> ብል ሃሳቡ ሙሉ በሙሉ ከሁኔታ እራሱን ያገለለ ይሆናል ፣ ምናልባት የየት ሀገር ገበሬ ለሚለው እንደ መልስ የቀረበ ሐረግ ተደርጎም ሊታይ ይችል ይሆናል ። ትንሽ ወደፊት ሄድ ብዬ ደሞ <ባለ ትራክተሩ የትግራይ ገበሬ > ብል ፣ አሁን ሃሳቡ ሙሉ በሙሉ ይቀየራል ። ድሃው የትግራይ ገበሬ ስል ፣ በሃዘን እና በልብ መነካት ያነበበው ተደራሲ ፣ ባለ ትራክተሩ የትግራይ ገበሬ ስል የሚኖረው ስሜት በፍጹም አንድ አይሆንም ። ከዚህ የምንረዳው ቃላትን በመቀያየር ብቻ ፣ የሰውን ስሜት ማብራት እና ማጥፋት እንደሚቻል ነው ። ያም ሆኖ እነዚህ ክፉ እና ደግ ገላጮች ፣ ለጥፋት የመረሩ ተደርገው ቢቀርቡ ወይም ደሞ ለመወደድ ያማሩ እና ማር የተቀቡ ሆነው ቢቀርቡ ፣ መሬት ላይ ያለውን እውነታ መለወጥ አይችሉም ፣ ይህ ማለት መዘዝ የላቸውም ማለት አይደለም ።
ለምሳሌ ህወሓት በረሃ በነበረ ጊዜ ደግሞ ደጋግሞ ያቀነቅን የነበረውን <ጨቋኝ ያማራ ስርዓት > የሚለውን አርፍተ ነገር እንመልከት ። ይህ አርፍተ ነገር በመጀመሪያ በህውሃት ሊህቃን ፣ በስም በነ አረጋዊ በርሄ እና በነገብሩ አስራት የተቀነቀነ ቀጥሎም በስብሐት ነጋና በመለስ ዜናዊ አማካኝነት <ጭሰኛውን > የትግራይ ሕዝብ በአማራ ላይ ለማስነሳት በጥናት የተወቀረ እና የተቀናበረ ነበር ፣ በፈረንጅኛ (It is an ideology by the revolutionary TPLF elites which was deliberately crafted to decive the peasants of Tigray )። እንደውም የመጀመሪያዎች የሞት ገፈት ቀማሾች የትግራይ ባላባቶች ነበሩ ፣ ይህንንም ግድያ ያቀነባበረው አረጋዊ በርሄ ስለመሆኑ አንድ ሽሬ እንዳ-ስላሴ ተወልዳ ያደገች ፣ በ 1971 አም ከትግራይ ወደ ሱዳን ኮብልላ የሄደች ፣ አረጋዊ በርሄ ሳን ሆዜ በመጣ ጊዜ ፣ እኔ እሷ ና አረጋዊ በርሄ ባንድ ጠረፔዛ ላይ ምሳ ከበላን በሗላ ፣ እሱ ወደ ውጭ አየር ለመውሰድ ሲወጣ ማርጀቱን እና በዚያን ጊዜ የነበረውን ተሰሚነቱን ፣ አፍሮውን እያስታወሰች የነገረችኝ ታሪክ ነበር ። ይህች ሴትዮ አረጋዊ በርሄ ጎረቤቷ እንደነበርም አጫውታኛለች ። ይህንን የወንጀል ታሪክም በወቅቱ የነገረችኝ ፣ አረጋዊ በርሄ ሳን ሆዜ በተዘጋጀው የኢትዮ- ኤርትራ የውይይት መድረክ ላይ በ 2010 እአአ በሳንሆዜ ተገኝቶ ያድረገውን ንግግር በመስማቷና ፣ እሷ በግሏ ከዔሪትራውያኖች ጋ የሚደረገውን ወዳጅነት ስለማትፈልገው ፣ በንዴት የአረጋዊ በርሄን ሀጥያት ተነፈሰችው ። ለኔ ጥሩ መረጃ ነበር !
ወደ ዋናው ቁም ነገር ልመለስ ። እንግዲህ እነ አረጋዊ በርሔ እና ስብሐት ነጋ < ጨቋኝ ያማራ ስርዓት> ብለው በጥላቻ ያጠቆሩት እና በኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም አያና ( ዘር ባባት ከተጠራ መንግስቱ ኦሮሞ ነው ) ይመራ የነበረው ስርዓት ፣ እንዲህ እንደ-ዛሬው ካንድ ጎሳ የመጣ ውህድ እና ቅምር ( chemistry) ያለው ሥርዓት አልነበረም ። በደም እና በስልጣን ተዋረድ ዛሬ በሕይወት ያሉ ዔርትራውያኖች ስንወያይ እንደመሰከሩልኝ በወቅቱ ለደርግ ተቀጥረው የዔርትራን ሕዝብ ያስጨርሱ የነበሩት የትግራይ ልጆች እንደነበሩ ነው ። ይህ ሁኔታ በ ጀነራል ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ብልህ የተሞላበት አመራር ( 1973-1974 ) ፣ በዔርትራውያን ወጣቶች ላይ ይደርስ የነበረው ግድያ እና በደል ጋብ ሲል ፣ ሻዕቢያን ተቀላቅለው ጫካ ወርደው የነበሩ የአስመራ ልጆች ወደ አስመራ ከተማ መመለስ ሲጀምሩ ፣ ይህንን የሰላምን እና የመረጋጋት ( የሁኔታ ለውጥ ) ለመቀልበስ እነ መለሰ ዜናዊና አቦይ ስብሐት ይህ ነው የማይባል ሚና እንደነበራቸው ሰምቻለሁ !
እና ያ < ጨቋኙ ያማራ ስርዓት> ( በወያኔኛ ምልከታ ) ላይመለስ ሄዷል ። የቀረው < ጨቋኙ ያማራ ስርዓት> ተመልሶ እንዳይመጣ የ <ጨቋኙን አማራ ስርዓት > ልጆች ማጥፋት ነው ። ይህ አርፍተ ነገር ለድሃው የትግራይ ገበሬ ልክ ነበር ፣ ዛሬም ልክ ነው ። ይህ አባባል በየአንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ልቦና ውስጥ ፣ ደም ስር ውስጥ ፣ አስተሳሰብ ውስጥ እንደ እምነት ሰርጾ ይታያል ። ስለዚህ ቁ ነገሩ እና መነሳት ያለበት ሃሳብ ፣ የትግራይ ገበሬ ድሃ ስለሆነ ( በአስተሳሰብም በሰብልም ) የፈለገውን የማሰብ መብት ሲኖረው ፣ ምንም እንዳይታሰብበት የሚያዝም ሌላ አባሪ መብትም ባለቤት የሆነ ይመስለኛል ።
ሌላ ምልከታ
አንድ ከትግራይ ሀጋር የመጣ የትግሬ ለማኝ ፣ የትግራይ ሕዝብ በስርዓቱ ተጠቃሚ ላለመሆኑ እንደ ማሳያ መቅረብ ይችላል ወይ ? ይህንን ጉዳይ የስነ ልቦናም ይሁን የምጣኔ ሀብት ምሁሮች እያመሳከሩ እንደ መርጫ ሃሳብ ቢጠቀሙበት ምናልባት ከላይ እንደገለጽኩት < ለጊዜው ትርጉም የሚሰጥ ይመስል ይሆናል ፣> ነባራዊ እውነታውን ግን አይገለብጠውም ፣ አይለውጠውም! የነጭ ለማኝ በ አማሪካ ጎዳናዎች ላይ ማየት ፣ ነጭ -በአማሪካ ስርዓት ውስጥ ተጠቃሚ አይደለም ብሎ የመከጀል አይነት ነገርም ይመስለኛል ። እርግጥ ህወሓት የትግራይን ገበሬ ለመጥቀም በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያፈሳል ፣ በበረሃ ላይ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ተክሎ የህዝቡን ሕይወት ለመቀየር ይተጋል ፣ አባይን ቤኒ ሻንጉል ግምዝ ጋ ገድቦ ነገ ለምትመሰረተው ታላቂቷ ትግራይ በሚታይ ሁኔታ ይተጋል፣ የትግራይ ልጆችን በ ( MIT ) ( MEKELE INSTITUTE ኦፍ TECHNOLOGY ) ጥራቱን በጠበቀ የትምህርት ደረጃ ያሰለጥናል ፣ ታዲያ ከነዚህ ግብዓቶች ባሻገር የተራበ ትግሬ ማየት ለምን ብርቅ ይሆናል ?
ችግሩ <ድሃው የትግራይ ገበሬ > የሚለው ገላጭ ላይ አይደለም ያለው ፣ ሃሳቤ የትግራይ ገበሬ የድርቅ እና የራብ ተጠቂ አልሆነም የሚልም አይደለም ፣ < እኔ > እያልኩ ያለሁት < ድሃው የትግራይ ገበሬ > ስለ ምንም ምክንያት ፣ እየራበውም ወያኔን ይደግፋል ። ልክ እዚህ አማሪካን ሀገር ያሉ አንዳድን ዘረኛ ነጮች ፣ ጎዳና ላይ ወድቀውም አንተ ጥቁር በመሆንህ ብቻ ሊንቁህ እንደምፈልጉት አይነት ። ስለዚህ የመነጋገሪያ ሃሳብ መሆን ያለበት የትግራይ ገበሬ ድህነት ሳይሆን ፣ እንደኔ ከኢትዮጵያዊነት አንጻር የትግራይ ገበሬ ሠብዓዊ ማንነት መሆን ያለበት ይመስለኛል ።
ድህነቱ ሃገራዊ ነው ፣ ጥላቻው እና ዘረኝነቱ ግን ክልላዊ ነው ። እየራበውም ያስራበውን የሚደግፍ ሥርአት ከራቡ አስበልጦ የሚወደው ነገር እስካለ ድረስ እኔ ስለሱ ሳወራ ስለ መራቡ ሳይሆኑ ከራቡ አስበልጦ ስለሚወደው ነገር ነው ፣ ነብሱን ስለሰጠለት ፍቅር ነው ። ከዚህ አንጻር ድሃው የትግራይ ገበሬ ብዬ እራሴን የማሳስትበት ገላጭ ቃላትም ይሁን ፣ ሰዋዊ ይሉኝታ የለኝም ። የትግራይ ገበሬ ድህነት ለኔ የሚታየኝ ፣ የትግራይ ገበሬ ለሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ቅን ሲሆን ብቻ ነው ። ለ ( political correctness ) ከፖለቲካ አንጻር ልክ ለመሆን ግን የተባለውን ሁሉ እያሉ መኖር ይቻላል ። እሱ እኔን አይመለከትም !