ሰውን በቀዬው ባይተዋር ማድረግና የትግራይ ተወላጆችን የኢኮኖሚ አቅም መገንባት – እውነተኛ ገጠመኝ
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
ያሳፍራል፤ ያሳዝናል፤ እውነተኛ ገጠመኝ //Girma Bekele
አንድ ኦሮሞ ወዳጄ –እንዲውም በጣም ቢቆይም ቀድሞ የኦሮሚያ ባለሥልጣን የነበረ፣ የመንግስት ሥራ ትቶ በግል ሥራ ኦሮሚያ ውስጥ ለዚያውም በተወለደበት አካባቢ ኢንቨስት ለማድረግ ፕሮፖዛሉን ይዞ ወደ ዞኑ ኢንቨስትመንት ቢሮ ይሄዳል፣ ያስገባል፡፡ የጠየቀውም ቦታ በማንም ተይዞ ያልነበረ መሆኑን ያረጋገጠ ቢሆንም እስኪጣራ ጠብቅ ይባላል፡፡ ውጤቱን እየተጠባበቀ ባለበት ቦታው ለትግራይ ተወላጅ የተሠጠ መሆኑ ይነገረዋል፡፡
ይህ ወዳጄ በእጅጉ አዝኖ ባለበት በስራ አጋጣሚ በእርሱ ትውልድ አካባቢ/ዞን በቅርብ ጊዜ ሄዶ ኢንቨስት ካደረገ ሌላ ትግሬ ጋር ይገናኛል፡፡ በጨዋታ ጨዋታ ተመሳሳይ ጉዳይ ሰውዬው እንደጀብድ ሲያነሳ እርሱም ስላጋጠመው በሌላ ወዳጁ አስመስሎ ያጫውተዋል፡፡በመጨረሻም ጉዳዩ የራሱ መሆኑን ይገልጽለታል፡፡ ምን ብለው ጥሩ ነው– ‹‹ የዞኑ ኢንቨስትመንት ውስጥ ያሉት ሁሉ የእኔ ሰዎች ናቸው እኮ አስቀድመን ተዋውቀንና ነግረሄኝ ቢሆን ኖሮ የምትለውን ቦታ ታገኝ ነበር፤ አሁንም የምትፈልገው ቦታ ካለ ላሰጥህ እችላለሁ፣ ….፡፡ ››
በዛሬ ላይ የትግሬ ተወላጅ መሆን ባደግንበት ከእኛ በላይ የበላይነትና የአዛኝነት አቅም ፣የባለቤትነትና የመሥራት መብት ያጎናጽፋል፡፡ ይህ መብትና አቅም የቸራቸው እኛን እንወክላለን ብለው የተደራጁ ፖለቲከኞች መሆኑን ስናውቅ ህመሙ እስከ አጥንት ዘልቆ ይሰማል፡፡ በዚህ ገጠመኝ ኦህዴድ ማለት ነው፡፡ ምን ኦሮሚ ዞን ወሰደህ አዲስ አበባስ ቢሆን እንደማትሉኝና ማስተር ፕላኑ ጋር እንደማትታገናኙት ልገምት ወይስ …..
ይህ አንድ ገጠመኝ ቢሆንም የሥርኣቱ አጠቃላይ መገለጫ ነው- ሰውን በቀዬው ባይተዋር ማድረግና የትግራይ ተወላጆችን የኢኮኖሚ አቅም ለመገንባት ተወላጁን ሁለተኛ ዜጋ ማድረግ፡፡ እባካችሁ የትግራይ ተወላጆች ይሉኝታ ይኑራችሁ፣ነገን አስቡ፤ ‹‹የእኛ ተወካዮችም›› ከራሳችሁ አልፋችሁ የወንድሞቻችሁን መብት ለማስረገጥ ተላላኪ እስከመቼ እንደምትሆኑ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡ በማን እንዳፈርኩና በማንስ እንዳዘንኩ ግልጽ ነው፡፡
በመጨረሻም ከትግራይ ውጪ ያሉት ትግሬዎች በቁጥር ስንት ናቸው ብሎ መጠየቅ ዛሬ ላይ ስህተት አይሆንም፤ ለምን ቢሉ ሰዎቹ ያልደረሱበት ቦታና የስራ ዘርፍ የለምኮ፤ በየቱም የስራ ዘርፍ ይሁን በአራቱም አቅጣጫ ዳርቻዎች ጭምር ብትሄዱ አይታጡምና፡፡
በቸር ያገናኘን፡፡