በትግራይ ለተከሰተው ረሃብ የመጣው እርዳታ ለተጎጂዎች ኣይደርስም ሲሉ ኣንድ ባለስልጣን ተናገሩ።
የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ።
Amdom Gebreslasie
“የእርዳታ እህሉ ወደ ተረጂው ህዝብ ልናደርሰው ኣልቻልንም” ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የምስራቃዊ ዞን ዋና ኣስተዳዳሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል።
ወይዘሮ ያለም ፀጋይ ያፍረጠረጠችው ሓቅ ” የእርዳታ እህሉ ወደ ተራበው ህዝብ ልናደርሰው ኣልቻልንም ከዚህ የተነሳ ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል። ይህም በመልካም ኣስተዳደር ያለብን ችግር ይበልጥ ኣደገኛነቱና ጥልቀቱ ኣሳሳቢ ደረጃ እንደደረሰ ያሳየናል” ብላለች። እኔም ይልመድሽ ብያለው።
ይህ ሓቅ ያፍረጠረጠችው ከምታስተዳድረው ምስራቃዊ ዞን የተውጣጡ ከ260 ባላይ የወረዳና የቀበሌ ስራ ኣስፈፃሚ ሓላፊዎች በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።
ይሄ ምስክርነት እንድናደምጥ የረዳን ሬድዮ ድምፂ ወያነ በዛሬ ጥዋት ዜና ዘባው ነው።
የወይዘሮ ያለም ምስክርነት ያተኮረው በወረዳና ቀበሌ ያለው የእርዳታ እህል ዝርፍያና ቅምያ ብቻ ቢሆንም እንደ ጅምር ግን የሚበረታታ ነው።
“የመጋዘን እጥረት፣ ለኣባይ ግድብ መስርያ” እየተባለ ለዱቄት ፋብሪካዎች የተሸጠው የእርዳታ እህል በተመለከተ ደግሞ ከትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪ እንጠብቃለን።
እናንተ ከጳጳሱ በላይ……ለምሆን የሚከጅላቹ የህወሓት ተስፈኛ፣ ኣሰፍሳፊ ትናንሽ የፌስቡክ ካድሬዎች ወደ ህዝባቹና ልባቹ ትመለሱ ዘንድ እንጠይቃለን።
እርዳታው በጣም ጥቂት ሆኖሳለ በእንቅርት ላይ ጀሮ ደገፍ እንደሚባለው “መጋዘን ጠበበ” ብሎው ከሚዘርፉ የክልል ባለስልጣናት ጀምሮ፣ የወረዳና የቀበሌ ኣላፊዎች የድርሻቸው ሲሚሞጨልፉበት በህዝቡ እጅ የሚደርሰው ጥቂት እህል ” ለመዳበርያ፣ ለማህበራት፣ ለኣምቡላንስ፣ ለደደቢት ዕዳ፣ ለጋዜጣ” ወዘተ እየተባለ ከእጁ ይነጠቃል።
ረሃብ ገዳይ ነውና በገዛ ህዝባቹ ሞት ኣትፍረዱ።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
IT IS SO.