የወያኔ የደህንነት ጽ/ቤቱ በአባላቶቹ ላይ አዲስ አሰራር ሊተገብር ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የስለላ እና ደህንነት አባሎቹ እየተሙለጨለጩበት ከባድ ትንቅንቅ ውስጥ ያለው እና ባለፈው ወር በግምገማ በተደጋጋሚ ሲታመስ የነበረው የወያኔ ደህንነት ቢሮ በአባላቶቹ ላይ አዲስ የአሰራር ስልት ሊዘረጋ መሆኑ ታውቋል::ባለፈው በተደረገው ግምገማ የተባረርት እንዲሁም ከደረጃቸው ዝቅ ያሉ እና ወደ ሌላ መስሪያ ቤቶች የተቀየሩ አባላቶችን በተመለከተ በድጋሚ ጉዳዩን አጢኖ ለማረም እና ለማስተካከል የታቀደ ሲሆን ይህም እቅድ ወያኔ በውስጧ ያለውን ችግር አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተታት የተባረሩ እና ከደረጃቸው ዝቅ ያሉ ስራቸው የተለወጠባቸው አባላት የቢሮውን ስራዎች እና ምስጢሮች ስለሚያውቁ ይበቀሉናል የሚል ፍራቻ ማደሩን ተጠቁሟል::

በፍርሃት እየራደ በፕሮፓጋንዳ ሃይል እና በምእራባውያን እርዳታ ስልጣን ላይ ያለው የወያኔ አገዛዝ በውስጡ የያዛቸው እና ቢፈነዱ ሊበታትኑት የሚችሉ ከባባድ የወታደራዊ እና የደህንነት ጉዳዮች ያሉ ቢሆንም ይህንን ደካማ ጎን ከፍተው መግባት ተቃዋሚዎች እንዳልቻሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::ምንጮቹ እንዳሉት በወታደሩ እና ደህንነቱ ክፍል ከፍተኛ የሆነ አለመተማመን እና ችግር እንዳለት ጠቁመው ባለፉት ወራቶች ይበደህንነት ሹሞች እና በወታደራዊ አዛዦች በኩል ሲደረጉ የነበሩ ስብሰባዎች እንዲሁም የአባላት ግምገማ በተጨማሪም የገጽታ ግንባታ ውይይቶች ለዚህ ምስክር መሆናቸውን ይገልጻሉ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬