በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ የረሃቡን መረጃ ለማርገብ የገጽታ ግንባታ ስብሰባዎች ሊደረጉ ነው::


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)– ከመከላከያ ሚኒስቴር የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ላለፉት ሁለት ቀናት የተሰበሰቡት የሕወሓት ጄኔራሎች ቡድን የሃገሪት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስለ ረሃቡ ያላቸውን መረጃ ለማርገብ እና ስለ ህዳሴው ልማት እና ዲሞክራሲ ያላቸውን ግንዛቤ ለማስፋት በሚል ሰበብ የገጽታ ግንባታ በየክፍሉ ስብሰባዎች በቡድን በቡድን እንዲደረጉ መወሰናቸው ተሰምቷል::

በአስቸኳይ በዚህ ሳምንት እንዲጀምር የሚደረገው ይህ ስብሰባ ሰርጎ ገቦች እንዳያሰናክሉ እና የሰራዊቱ አባላትን በአጉል ስርኣት አልበኝነት እንዳይወሰውሱ ስብሰባዎች ላይ ከባድ ቁጥጥር እንዲደረግ እና በየቡድኑ ሁኔታዎችን ቤንቃት የሚከታተሉ ወታደራዊ ደህንነቶች እንዲመደቡ እንዲሁም ለቡድን አወያይ የሚሆኑ አባላት በልስላሴ እና በሰላማዊ ባህርይ ጸረ ሕዝቦችን ለመለየት በሚያስችል ዘዴ ተመሳስለው ስብሰባውን እንዲመሩ ሲባል ቡድኑ 30 የሰራዊት አባላት ማቀፍ እንዳለበት መመሪያ ተላልፏል::

ይህ በበየእዙ ካሉ በየካምፑ ለሚኖሩ የሰራዊት አባላት የሚደረገው የገጽታ ግንባታ ስብሰባ በከተማ ለሚገኡ የሰራዊቱ አባላት እና ለአየር ሃይል አባላት እደማይሰጥ ከወዲሁ ሲታወቅ በረሃቡ ዙሪያ ያለውን መረጃ ለማለዘብ ግን ለነዚሁ ክፍሎች ግልጽ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የመከላከያ ሚኒስቴር ምንጮች ለምንሊክሳልሳዊ ተናግረዋል::በመከላከታ ስራዊቱ ውስጥ አለመተማመን እና ከፍተኛ የዘረኝነት ጫና ከመኖሩም በላይ የአንድ ብሄር ሰዎች በበላይነት እና በጥቅም ተሳስረው የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እያጭበረበሩ እንደሚገኝ ይታወቃል:: ጥቅማ ጥቅም እና ማእረግ ለማግኘት አዳጋች የሆነበት የሰራዊቱ አባላት ጥያቄዎችን ቢያነሳም በአደርባዮች እና በሆድ አደሮች እየታፈነ ለሐሓት ሰው በላዎች ተላልፎ ይሰጣል::

በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን አሁን በሃገሪቱ ከተከሰተው ረሃብ እና ድርቅ ጋር ተደምሮ ከፍተኛ አደጋ ይፈጥርብኛል ብሎ ያሰበው ወያኔ ያለውን ሃይል እና ገንዘብ ሁሉ በመጠቀም መረጃዎችን ለማዳፈን እና ምንም እንቅስቃሴ እንዳሌለ ለማስመሰል ደፋ ቀና እያል በመስራት ላይ ሲሆን በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ላይ የሃስት ዶክመንተሪዎችን በመስራት በችግር የቀጨጨችውን አገር የለማች ለማስመሰ ከመጣሩም በላይ ወገን እየተራበ በየቦታው የሚደገሱ የፓርቲ ድግሶች ለድርቁ እና ረሃቡ አቅም ግንባታ እንደሆኑ ለማኝበርበር በመሰበክ ላይ ይገኛሉ:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

Minilik Salsawi's photo.